Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ቲቶ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንዲሁም አሮጊቶች በአኗኗራቸው የተከበሩ እንዲሆኑ፣ በጎ የሆነውን የሚያስተምሩ እንጂ የሰው ስም የሚያጠፉ ወይም በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ አስተምራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በጠባያቸው የተከበሩ እንዲሆኑ እንጂ ሐሜተኞችና፥ የመጠጥ ሱሰኞች እንዳይሆኑና መልካሙን ትምህርት እንዲያስተምሩ ምከራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar




ቲቶ 2:3
13 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱም ዐመ​ፅን ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም፥ ምኞ​ት​ንም፥ ቅሚ​ያ​ንም፥ ቅና​ት​ንም የተ​መሉ ናቸው፤ ምቀ​ኞች፥ ነፍሰ ገዳ​ዮች፥ ከዳ​ተ​ኞች፥ ተን​ኰ​ለ​ኞች፥ ኩሩ​ዎች፥ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ግብ​ራ​ቸ​ው​ንም ያከፉ ናቸው።


ለቅ​ዱ​ሳ​ንም እን​ደ​ሚ​ገባ በጌ​ታ​ችን ተቀ​በ​ሉ​አት፤ እር​ስዋ ለብ​ዙ​ዎች፥ ለእ​ኔም ረዳት ናትና፤ ለች​ግ​ራ​ች​ሁም በፈ​ቀ​ዳ​ች​ሁት ቦታ መድ​ቡ​አት።


ነገር ግን ለቅ​ዱ​ሳን እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው፥ ዝሙ​ትና ርኵ​ሰት ሁሉ ወይም ቅሚያ አይ​ሰ​ማ​ባ​ችሁ።


እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።


እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥


ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውሃ ብቻ አትጠጣ።


ኤጲስቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥


ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።


መም​ህ​ራን ልት​ሆኑ ሲገ​ባ​ችሁ፥ ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በት​ም​ህ​ርት ላይ የቈ​ያ​ችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃ​ሉን መጀ​መ​ሪያ ትም​ህ​ርት ሊያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ወተ​ት​ንም ሊግ​ቱ​አ​ችሁ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ ምግ​ብ​ንም አይ​ደ​ለም።


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos