Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ደግሞም የመጀመሪያው አውሬ ምስል መናገር እንዲችል ለምስሉ እስትንፋስ ለመስጠትና ለዚህም ምስል የማይሰግዱ ሁሉ እንዲገደሉ ለማድረግ ሥልጣን ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የአውሬው ምስል እንዲናገርም ሆነ ለአውሬው ምስል የማይሰግዱትን እንዲያስወግዳቸው ለአውሬው ምስል እስትንፋስ እንዲሰጠው ተፈቀደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሁለተኛው አውሬ ለመጀመሪያው አውሬ ምስል የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን ተሰጠው፤ የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠውም ምስሉ ለመናገር እንዲችልና ለእርሱ የማይሰግዱት ሁሉ እንዲገደሉ ያደርግ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 13:15
25 Referencias Cruzadas  

ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።


የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”


ሦስተኛም መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥


በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።


በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።


እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ስእ​ለ​ቴን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ጣ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”


የውሃውም መልአክ “ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ! ቅዱስ ሆይ! እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤


ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።


እንጨቱን፦ ንቃ፥ ዲዳውንም ድንጋይ፦ ተነሣ ለሚለው ወዮለት! በውኑ ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ ምንም እስትንፋስ የለበትም።


አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።


በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios