እነሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶቅና ከእርሱም ጋር ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት አስቀመጡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ከከተማዪቱ ፈጽሞ እስኪያልፉ ድረስ አብያታር ወጣ።
2 ሳሙኤል 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአኪጦብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአቤሜሌክም ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ። አሳም ጸሓፊ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሓፊ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም የአሒጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፥ ሠራያ ጸሓፊ ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሒጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቤሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሠራያ ደግሞ ጸሐፊ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአኪጦብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአቢሜሌክም ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፥ ሠራያም ጸሐፊ ነበረ፥ |
እነሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶቅና ከእርሱም ጋር ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት አስቀመጡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ከከተማዪቱ ፈጽሞ እስኪያልፉ ድረስ አብያታር ወጣ።
አርካዊው ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፥ “አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፤ እኔ ግን እንዲህና እንዲያ መክሬአለሁ።
ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፥ ካህኑንም ሳዶቅን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ አገልጋይህንም ሰሎሞንን አልጠራም።
በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
ሕዝቅያስንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም ጸሓፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ።
ዳዊትም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፥ ሌዋውያንንም፥ ኡርኤልን፥ ዓሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሰማያን፥ ኤሊኤልን፥ አሚናዳብንም ጠርቶ፦
ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥
ለእስራኤልም ልጆች ይነግራቸው ዘንድ አገልጋዩ ሙሴን እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ።
የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የመራዩት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ፤
ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ በመጽሐፉ አንበበ።
“ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዐት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።