2 ሳሙኤል 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ተባለች። ከተማዋንም ዙሪያዋን እስከ ዳርቻዋ ድረስ ቀጠራት፤ ቤቱንም ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በምሽጉ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራው። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ከተማ ብሎ ጠራት። ዳዊትም ዙሪያዋን ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ ቀጠራት። |
በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ።
ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣት ዘንድ አልወደደም፤ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባት።
እርሱም ያደረገው ይህ ነው በንጉሡ በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎሞንም በዳርቻ ያለ ቅጥርንና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።
ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
አገልጋዮቹም የኢያሙሃት ልጅ ኢያዜክርና የሳሜር ልጅ ኢያዛብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ ልጁም አሜስያስ በፋንታው ነገሠ።
ሕዝቅያስም ሰውነቱን አጽናና፤ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊትም ከተማ የሚያወጣውን በር አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ አዘጋጀ።
የመሴፋም ገዢ የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደነውም፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፤ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የመዋኛ ቅጥር ሠራ።
እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰቂማንም ሰዎች፥ የመሐሎንንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይሆን ከሰቂማ ሰዎች ከመሐሎንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤሜሌክንም ትብላው።”
የሰቂማም ሰዎች ሁሉ፥ የመሐሎንም ቤት ሁሉ ተሰበሰቡ፤ ሄደውም በሰቂማ በዐምዱ አጠገብ ባለው የወይራ ዛፍ በታች አቤሜሌክን አነገሡ።