Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሰ​ቂ​ማም ሰዎች ሁሉ፥ የመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት ሁሉ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሄደ​ውም በሰ​ቂማ በዐ​ምዱ አጠ​ገብ ባለው የወ​ይራ ዛፍ በታች አቤ​ሜ​ሌ​ክን አነ​ገሡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሴኬምና የቤት ሚሎ ገዦች በሙሉ አቢሜሌክን ለማንገሥ ሴኬም ውስጥ በዐምዱ አጠገብ ካለው የባሉጥ ዛፍ ሥር ተሰበሰቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሴኬምና የቤትሚሎ ነዋሪዎች በሙሉ አቤሜሌክን ለማንገሥ ሴኬም ውስጥ በዐምዱ አጠገብ ካለው የባሉጥ ዛፍ ሥር ተሰበሰቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚያን በኋላ የሴኬምና የቤትሚሎ ሕዝብ በአንድነት ተሰብስበው፥ በሴኬም ወደሚገኘው ወደተቀደሰው ወርካ ዛፍ ሄዱ፤ በዚያም አቤሜሌክን አነገሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሴኬምም ሰዎች ሁሉ ቤትሚሎም ሁሉ ተሰበሰቡ፥ ሄደውም በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በአድባሩ ዛፍ በታች አቤሜሌክን አነገሡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 9:6
8 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ወደ ሰቂማ መጥ​ተው ነበ​ርና ሮብ​ዓም ወደ ሰቂማ ሄደ።


ከዚ​ህም በኋላ እስ​ራ​ኤል በሙሉ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከግ​ብፅ እንደ ተመ​ለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸን​ጎ​አ​ቸው ጠሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሡት። ከብ​ቻው ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ነገድ በቀር የዳ​ዊ​ትን ቤት የተ​ከ​ተለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሰቂ​ማን ሠርቶ በዚያ ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከዚያ ወጥቶ ፋኑ​ኤ​ልን ሠራ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።


ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት።


ወደ አባ​ቱም ቤት ወደ ኤፍ​ራታ ገባ፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን የይ​ሩ​በ​ኣ​ልን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገደ​ላ​ቸው፤ ትንሹ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ ኢዮ​አ​ታም ግን ተሸ​ሽጎ ነበ​ርና ተረፈ።


ይህ​ንም ነገር ለኢ​ዮ​አ​ታም በነ​ገ​ሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድም​ፁ​ንም አን​ሥቶ አለ​ቀሰ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “የሰ​ቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይስ​ማ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos