Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን፥ ሜሎ​ን​ንም፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር፥ አሶ​ር​ንም፥ መጊ​ዶ​ንም፥ ጋዜ​ር​ንም ይሠራ ዘንድ ሠራ​ተ​ኞ​ችን መል​ምሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ አሦርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጕልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ የኢየሩሳሌምን ቅጽር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ ሞልተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ለመሥራት የሚገደዱ ሠራተኞች ነበሩ፤ እንዲሁም ሐጾር፥ መጊዶና ጌዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችንም እንዲሠሩለት አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ለሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ የኢየሩሳሌምን ቅጽር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ ሞልተው ያስተካከሉለት የጒልበት ሥራ ለመሥራት የሚገደዱ ሠራተኞች ነበሩ፤ እንዲሁም ሐጾር፥ መጊዶና ጌዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችንም እንዲሠሩለት አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት፥ ሚሎንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ ሐጾርንም፥ መጊዶንም፥ ጌዝርንም ይሠራ ዘንድ ገባሮችን መልምሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 9:15
34 Referencias Cruzadas  

የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ሰሎ​ሞን ወደ ሠራ​ላት ወደ ቤቷ አመ​ጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎ​ንን ሠራት።


ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገባ​ሮ​ቹን መርጦ አወጣ፤ የገ​ባ​ሮ​ቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ።


ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።


በይ​ሳ​ኮ​ርና በአ​ሴር መካ​ከል ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጌ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ የመ​ፌታ ሦስ​ተኛ እጅና መን​ደ​ሮ​ችዋ ለም​ናሴ ነበሩ።


አር​ሜት፥ አራ​ሂን፥ አሦር፥


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ሶር ንጉሥ ኢያ​ቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማሮን ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ስሚ​ዖን ንጉሥ፥ ወደ አዚ​ፍም ንጉሥ፥


ኤፍ​ሬ​ምም በጋ​ዜር የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በጋ​ዜር ተቀ​መጡ፤ ገባ​ሮ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።


በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።


በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል።


ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤት የሠ​ራ​በት ሃያ ዓመት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥


ከዚ​ህም በኋላ በጋ​ዜር ላይ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት እንደ ገና ሆነ፤ ያን​ጊ​ዜም ኡሳ​ታ​ዊው ሴቦ​ቃይ ከኀ​ያ​ላን ወገን የነ​በ​ረ​ውን ሲፋ​ይን ገድሎ ጣለው።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ያሉ​ትን የመ​ማ​ፀ​ኛ​ውን ከተ​ሞች ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ደግ​ሞም ጋዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ያን ባየ ጊዜ በአ​ት​ክ​ልት ቤት መን​ገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እር​ሱ​ንም ደግሞ አል​ተ​ወ​ውም” ብሎ ተከ​ተ​ለው። በይ​ብ​ላ​ሄ​ምም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በጋይ አቀ​በት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ወጋው። ወደ መጊ​ዶም ሸሸ፥ በዚ​ያም ሞተ።


እር​ሱም ያደ​ረ​ገው ይህ ነው በን​ጉሡ በሰ​ሎ​ሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዳ​ርቻ ያለ ቅጥ​ር​ንና የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ ያል​ቻ​ሉ​ትን፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አድ​ርጎ መለ​መ​ላ​ቸው።


ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት ሁለ​ቱን ቤቶች በሠ​ራ​በት በሃያ ዓመት ውስጥ፥


በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።


ከቤ​ት​ሳን ጀምሮ እስከ አቤ​ል​ም​ሖ​ላና እስከ ዮቅ​ም​ዓም ማዶ ድረስ በታ​ዕ​ና​ክና በመ​ጊዶ በጸ​ር​ታ​ንም አጠ​ገብ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በታች ባለው በቤ​ት​ሳን ሁሉ የአ​ሒ​ሉድ ልጅ በዓና ነበረ፤


እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”


የሰ​ቂ​ማም ሰዎች ሁሉ፥ የመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት ሁሉ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሄደ​ውም በሰ​ቂማ በዐ​ምዱ አጠ​ገብ ባለው የወ​ይራ ዛፍ በታች አቤ​ሜ​ሌ​ክን አነ​ገሡ።


ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሦር በነ​ገ​ሠው በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ይቀ​መጥ ነበረ።


ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።


ሰሎ​ሞ​ንም ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን አማች ሆነ፤ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ አገባ፤ ቤቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ያለ​ውን ቅጥር ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አም​ጥቶ አስ​ገ​ባት።


“አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አሁ​ንም አንተ ጽኑ​ውን የአ​ባ​ት​ህን አገ​ዛዝ፥ በላ​ያ​ች​ንም የጫ​ነ​ውን የከ​በ​ደ​ውን ቀን​በር አቃ​ል​ል​ልን፤ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን።”


ወደ ምዕ​ራ​ብም እስከ የፍ​ሌ​ጣ​ው​ያን ዳርቻ እስከ ታች​ኛው ቤቶ​ሮን ዳርቻ ድረስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios