La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 8:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊጋ​ጠም ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አካዝያስም ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋራ ሆኖ በሶርያ ንጉሥ በአዛሄል ላይ ለመዝመት ወደ ራሞት ገለዓድ ሄደ፤ ሶርያውያንም በዚያ ኢዮራምን አቈሰሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሶርያው ንጉሥ አዛሄል ላይ በታወጀው ጦርነት፥ ንጉሥ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ተባባሪ በመሆን ዘመተ፤ የሁለቱም ነገሥታት ሠራዊት ከሶርያውያን ሠራዊት ጋር በገለዓድ በምትገኘው በራሞት ጦርነት በገጠመ ጊዜ ኢዮራም በውጊያው ላይ ቆሰለ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሶርያው ንጉሥ አዛሄል ላይ በታወጀው ጦርነት፥ ንጉሥ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ተባባሪ በመሆን ዘመተ፤ የሁለቱም ነገሥታት ሠራዊት ከሶርያውያን ሠራዊት ጋር በገለዓድ በምትገኘው በራሞት ጦርነት በገጠመ ጊዜ ኢዮራም በውጊያው ላይ ቈሰለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከአክዓብም ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገልዓድ ሊጋጠም ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 8:28
18 Referencias Cruzadas  

ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዘመቱ።


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞ​ዓብ ላይ ለሰ​ልፍ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” ብሎ፤ ላከ። እር​ሱም፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አን​ተም እንደ እኔ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶ​ቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለ።


ከዚ​ህም በኋላ በነ​ጋው ለሐፍ ወስዶ በውኃ ነከ​ረው፤ በፊ​ቱም ላይ ሸፈ​ነው፥ ሞተም። አዛ​ሄ​ልም በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ንጉ​ሡም ኢዮ​ራም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ። የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ኢዮ​ራም ታምሞ ነበ​ርና የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ሊያ​የው ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።


ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።


እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።


ንጉሡ ኢዮ​ራም ግን ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ልሶ ነበር። ኢዩም ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከእኔ ጋር ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለሞት መስ​ጠት ትች​ላ​ላ​ች​ሁን? እን​ግ​ዲህ ማንም የሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ችሁ፥ ከከ​ተ​ማ​ች​ሁም የሚ​ወጣ እን​ዳ​ይ​ኖ​ርና በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እን​ዳ​ያ​ወራ ተጠ​ን​ቀቁ።”


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ አረ​ማ​ው​ያን የሶ​ርያ ሰዎች በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይታ​ከም ስለ ነበረ ኢዩ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ። ጠን​ካ​ራና ኀይ​ለኛ ሰው ነበ​ርና፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ራ​ምን ለማ​የት ወርዶ ነበር።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


በም​ክ​ራ​ቸ​ውም ሄደ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከአ​ክ​ዓብ ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።


ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤