2 ነገሥት 8:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተረፈውም የኢዮራም ነገር ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢዮራም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮራም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮራም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተረፈውም የኢዮራም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
የቀረውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራዎቹም ሁሉ፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥት ታሪክ የተጻፈ አይደለምን? ነገር ግን በሸመገለ ጊዜ እግሮቹ ታመሙ።
የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ኀይሉም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውን እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማዪቱ እንዳመጣ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
የምናሴም የቀረው ነገርና የሠራው ሥራ ሁሉ፥ ያደረገውም ኀጢአት፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
ኢዮራምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በአባቱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በፋንታውም ልጁ አካዝያስ ነገሠ።