ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
2 ነገሥት 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ሆይ፤ በፊትህ በታማኝነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፣ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ዐስብ፤” ሕዝቅያስም አምርሮ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እግዚአብሔር ሆይ! በታማኝነትና በቅንነት እንዳገለገልኩህ፥ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር ለማድረግ ዘወትር እጥር እንደ ነበር ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ!” እያለ በመጸለይ ምርር ብሎ አለቀሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ሆይ! በታማኝነትና በቅንነት እንዳገለገልኩህ፥ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር ለማድረግ ዘወትር እጥር እንደ ነበር ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ!” እያለ በመጸለይ ምርር ብሎ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ።” ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ። |
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ ሄኖክም ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ።
እግዚአብሔርም ኖኅን፥ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዊቱን ሁሉ፥ እንስሳውንም ሁሉ፥ አዕዋፍንም ሁሉ፥ የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፋስን አመጣ፤ ውኃውም ጐደለ፤
ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር አልነበረም። ከባዕድ ያገባቸው ሚስቶቹም ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን መለሱት።
ነገር ግን በኮረብቶች ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላራቀም፤ የአሳ ልብ ግን በዘመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ነበረ።
ይኸውም እግዚአብሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በእውነት ቢሄዱ ከእስራኤል ዙፋን ሰው አይጠፋም’ ብሎ የተናገረውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።
ሰሎሞንም አለ፥ “እርሱ በፊትህ በእውነትና በጽድቅ፥ በልብም ቅንነት ከአንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአባቴ ከባሪያህ ከዳዊት ጋር ታላቅ ቸርነት አድርገሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን አቈይተህለታል።
እንዲህም አለ፥ “የእስራኤል አምላክ አቤቱ! በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር አንተን የሚመስል አምላክ የለም፤ በፍጹም ልቡ በፊትህ ለሚሄድ ባሪያህ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥
እንደ ዛሬው ቀን በሥርዐቱ እንሄድ ዘንድ፥ ትእዛዙንም እንጠብቅ ዘንድ፥ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ልባችን ፍጹም ይሁን።”
ዳዊትም አባትህ በጽድቅ፥ በንጹሕ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዐቴንም ሕጌንም ብትጠብቅ፥
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ሌዋውያኑንም ራሳቸውን እንዲያነጹ፥ መጥተውም በሮቹን እንዲጠብቁ፥ የሰንበትንም ቀን እንዲቀድሱ ነገርኋቸው። “አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ደግሞ አስበኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ራራልኝ” አልሁ።
በየጊዜውም ዕንጨት ለሚሸከሙ ሰዎች ቍርባን፥ ለበኵራቱም ሥርዐት አደረግሁ። “አምላካችን ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።”
አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
እግዚአብሔርም ሰይጣንን አለው፥ “በባሪያዬ በኢዮብ ላይ የምታስበው ነገር እንዳይኖር ተጠንቀቅ! በምድር ላይ እንደ እርሱ ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ሰው የለምና።”
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።