ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፥ “እግዚአብሔር በጐበኛችሁ ጊዜ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማላቸው።
2 ነገሥት 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮራውያንና በዘበኞች ላይ ያሉትን የመቶ አለቆች ወሰደ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አገባቸው፤ ከእነርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አማላቸው፤ የንጉሡንም ልጅ አሳያቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ ካራውያንንና ዘብ ጠባቂዎቹን የሚያዝዙትን የመቶ አለቆች እርሱ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አደረገ። ከእነርሱም ጋራ ቃል ኪዳን በማድረግ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አስማላቸው፤ ከዚያም የንጉሡን ልጅ አሳያቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኃላፊዎች ወደ ሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኀላፊዎች ወደሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ በካራውያንና በዘበኞች ላይ ያሉትን የመቶ አለቆች ወሰደ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አገባቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አማላቸው፤ የንጉሡንም ልጅ አሳያቸው። |
ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፥ “እግዚአብሔር በጐበኛችሁ ጊዜ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማላቸው።
ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
ንጉሡም ሮብዓም በፋንታው የናስ ጋሾችን ሠራ፤ በፊቱም ለሚሮጡና የንጉሥን ቤት ደጅ ለሚጠብቁ የዘበኞች አለቆች ሰጣቸው።
አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ፥ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።
ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ፥ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፤ ደግሞም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ።
መቶ አለቆቹንና ኮራውያንን፥ ዘበኞችንና የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰዳቸው፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወጣው፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን አስቀመጡት።
መቶ አለቆችም ብልሁ ዮዳሄ ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ በሰንበት ይገቡ የነበሩትን፥ በሰንበትም ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።
ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ፥ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አልጠገናችሁም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ” አላቸው።
ንጉሡም በዓምደ ወርቁ አጠገብ ቆሞ እግዚአብሔርን ይከተሉ ዘንድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩንም ሥርዐቱንም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይጠብቁ ዘንድ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።
የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ወንድሞቻቸው ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ለእግዚአብሔር ቤትም ማገልገል ሥራ እጅግ ብቁዎች ሰዎች ነበሩ።
አሁንም የቍጣውን መቅሠፍት ከእኛ እንዲመልስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን አደርግ ዘንድ በልቤ አስቤአለሁ።
በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ።
እነርሱም፥ “እንመልስላቸዋለን፤ ከእነርሱም ምንም አንሻም፤ እንደተናገርህ እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ እንደዚህ ነገር ያደርጉ ዘንድ አማልኋቸው።
ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ አለቆቻችንም፥ ሌዋውያኖቻችንም፥ ካህናቶቻችንም ያትሙበታል።”
ከዚህም በኋላ የቤተ መቅደሱ ሹም ከሎሌዎቹ ጋር ሔዶ አባብሎ አመጣቸው፤ በግድም አይደለም፤ በድንጋይ እንዳይደበድቧቸው ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።