Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ጌታዬ፥ ይፈ​ል​ግህ ዘንድ ያል​ላ​ከ​በት ሕዝብ ወይም መን​ግ​ሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አን​ተን እን​ዳ​ላ​ገኙ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ አንተን ለመፈለግ መልእክተኛ ያልላከበት ሕዝብና መንግሥት የለም፤ የትኛውም ሕዝብ ሆነ መንግሥት አንተ በዚያ አለመኖርህን ባስታወቀው ጊዜ ሁሉ አንተን አለማግኘቱን ለማረጋገጥ ያስምለው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርክን ባስታወቀው ቍጥር ንጉሥ አክዓብ የአንተን አለመኖር በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ጠይቆአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርክን ባስታወቀው ቊጥር ንጉሥ አክዓብ የአንተን አለመኖር በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ጠይቆአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም ‘በዚህ የለም፤’ ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 18:10
20 Referencias Cruzadas  

በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።


ንጉ​ሡም ጸሓ​ፊ​ውን ባሮ​ክ​ንና ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ይይዙ ዘንድ የን​ጉ​ሡን ልጅ ይረ​ሕ​ም​ኤ​ል​ንና የዓ​ዝ​ር​ኤ​ልን ልጅ ሠራ​ያን የዓ​ብ​ድ​ኤ​ል​ንም ልጅ ሰሌ​ም​ያን አዘዘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰወ​ራ​ቸው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤


ኀጢ​አ​ተ​ኞች እነሆ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረ​ዋ​ልና፥ ፍላ​ጻ​ቸ​ው​ንም በአ​ው​ታር አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋ​ልና፥ ልበ ቅኖ​ቹን በስ​ውር ይነ​ድፉ ዘንድ።


ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።


ሴት​የ​ዋም፥ “አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በማ​ድጋ ካለው ከእ​ፍኝ ዱቄት በማ​ሰ​ሮም ካለው ከጥ​ቂት ዘይት በቀር እን​ጀራ የለ​ኝም፤ እነ​ሆም፥ ጥቂት እን​ጨት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ ሄጄም ለእ​ኔና ለልጄ እጋ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ተ​ነ​ውም እን​ሞ​ታ​ለን” አለ​ችው።


“ተነ​ሥ​ተህ በሲ​ዶና አጠ​ገብ ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰራ​ፕታ ሂድ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጥ፤ እነ​ሆም፥ ትመ​ግ​ብህ ዘንድ አን​ዲት መበ​ለት አዝ​ዣ​ለሁ።”


ሄዶም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ትይዩ ባለው በኮ​ራት ፈፋ ተቀ​መጠ።


አሁ​ንም ያጸ​ናኝ፥ በአ​ባ​ቴም በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ያስ​ቀ​መ​ጠኝ፥ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ቤትን የሠ​ራ​ልኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዛሬ አዶ​ን​ያስ ፈጽሞ ይገ​ደ​ላል።


ንጉ​ሡም እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳ​ነኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን ጠርቶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አንተ በፊቴ ጻድ​ቅና ደግ ነህ፤ ከእ​ኔም ጋር በጭ​ፍ​ራው በኩል መው​ጣ​ት​ህና መግ​ባ​ትህ በፊቴ መል​ካም ነው፤ ወደ እኔ ከመ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አን​ዳች ክፋት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ብ​ህም፤ ነገር ግን በአ​ለ​ቆች ዘንድ አል​ተ​ወ​ደ​ድ​ህም።


አብ​ድ​ዩም አለ፥ “እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን እን​ዲ​ገ​ድ​ለኝ በአ​ክ​ዓብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠኝ ዘንድ ምን በደ​ልሁ?


አሁ​ንም፥ እነሆ፦ ሂድ፥ ኤል​ያስ አለ ብለህ ለጌ​ታህ ንገር ትለ​ኛ​ለህ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


አለ​ቆ​ቹም ባሮ​ክን፥ “አን​ተና ኤር​ም​ያስ ሂዱ፤ ተሸ​ሸጉ፤ ወዴ​ትም እንደ ሆና​ችሁ ማንም አይ​ወቅ” አሉት።


እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios