Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የአገልጋዮቹ ሹሙም ከወታደሮቹ ጋራ ሄዶ፣ ይዞ አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግሯቸው ስለ ፈሩ በኀይል ሳያስገድዱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፤ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ወዲያውኑ የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃና ሎሌዎቹ ሄደው አመጡአቸው፤ ያመጡአቸውም በኀይል ሳይሆን በማግባባት ነው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግራቸው በመፍራት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፥ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 5:26
13 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም እጅግ ያከ​ብ​ሩ​አ​ቸው ነበረ። ከሌ​ሎ​ችም ይቀ​ር​ባ​ቸው ዘንድ አንድ ስን​ኳን የሚ​ደ​ፍር አል​ነ​በ​ረም።


እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደሱ ሹምም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጥ​ተው፥ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ይፈ​ሩ​አ​ቸው ነበር።


ያን ጊዜም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎች ሊይ​ዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነ​ርሱ እንደ መሰለ ዐው​ቀ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ፈሩ​አ​ቸው።


ከሰው ነው ብን​ለ​ውም ሕዝቡ ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል፤ ሁሉም ዮሐ​ንስ ነቢይ እንደ ሆነ አም​ነ​ው​በ​ታ​ልና።


ነገር ግን “በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን፤” አሉ።


‘ከሰው’ ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን” አሉ።


ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።


ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።


ሄዶም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከታ​ላ​ላ​ቆች ጋር እር​ሱን አሳ​ልፎ እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ተነ​ጋ​ገረ።


አሽ​ከ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም መጥ​ተው በወ​ኅኒ ቤት አጡ​አ​ቸ​ውና ተመ​ል​ሰው ነገ​ሩ​አ​ቸው።


አንድ ሰውም መጥቶ፥ “ያሰ​ራ​ች​ኋ​ቸው እነ​ዚያ ሰዎች እነሆ፥ በቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ናቸው፤ ቆመ​ውም ሕዝ​ቡን ያስ​ተ​ም​ራሉ” ብሎ ነገ​ራ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios