Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ኢዮ​አ​ስም ካህ​ኑን ዮዳ​ሄ​ንና ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች ስለ ምን አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁም? ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ገን​ዘቡ ለቤቱ መጠ​ገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚ​ያ​መ​ጡት ሰዎች አት​ቀ​በሉ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ ንጉሡ ኢዮአስ ካህኑን ዮዳሄንና ሌሎቹን ካህናት ጠርቶ፣ “በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ያላደሳችሁት ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፤ ቀጥሎም፣ “ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ለማደስ ይዋል እንጂ ከገንዘብ ያዦች አትቀበሉ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮአስ እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ካህናቱ አልጠገኑትም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 12:7
9 Referencias Cruzadas  

ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኢዮ​አዳ በረታ፤ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የኢ​ዮ​ራ​ምን ልጅ አዛ​ር​ያ​ስን፥ የኢ​ዮ​አ​ና​ንም ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን፥ የዖ​ቤ​ድ​ንም ልጅ አዛ​ር​ያን፥ የኢ​ዳ​ኢ​ንም ልጅ መዓ​ስ​ያን፥ የዘ​ካ​ር​ያ​ስ​ንም ልጅ ኤሊ​ሳ​ፋ​ጥን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ።


ኢዮ​አ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ አሁን ባለ​በት መቶ እጥፍ ይጨ​ምር፤ የጌ​ታዬ የን​ጉሥ ዐይ​ኖ​ችም ይዩ፤ ሁሉም የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በደል ይሆን ዘንድ ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል?” አለ።


ካህኑ ዮዳሄ ያስ​ተ​ም​ረው በነ​በረ ዘመን ሁሉ ኢዮ​አስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮ​ራ​ው​ያ​ንና በዘ​በ​ኞች ላይ ያሉ​ትን የመቶ አለ​ቆች ወሰደ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አማ​ላ​ቸው፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው።


ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮ​አስ እስከ ሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ካህ​ናቱ አል​ጠ​ገ​ኑ​ትም ነበር።


ካህ​ና​ቱም “ከሕ​ዝቡ ገን​ዘ​ቡን አን​ወ​ስ​ድም፤ በቤ​ቱም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን አን​ጠ​ግ​ንም፥” ብለው ተስ​ማሙ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም ይላል ብሎ ተናገረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios