2 ቆሮንቶስ 11:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ያደረግሁትም ቢሆን፥ የማደርገውም ቢሆን፥ እነርሱ እንደ እኛ የሚመኩበትን ያገኙ ዘንድ፥ ምክንያት የሚሹትን ምክንያት አሳጣቸው ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኛ ጋራ እኩል ለመሆን በሥራቸው እየተመኩ ቀን የሚጠብቁትን ሰዎች ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደ ፊትም አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በሚመኩበት ሥራ ከእኛ እኩል በአቻነት ለመቆጠር የሚፈልጉ ሰዎችን ምክንያት ለማሳጣት፥ አሁን የማደርገውን ወደፊትም እገፋበታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ሌሎች ሐዋርያት “እኛም እንደ እነርሱ እንሠራለን” እያሉ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደፊትም ደግሞ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በዚያ በሚመኩበት እንደ እኛ ሆነው ሊገኙ፥ ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ። |
በእኛ ሹመት ሌላ የሚቀድመን ከሆነ የሚሻላችሁን እናንተ ታውቃላችሁ፤ እኔ ይህን አልፈለግሁትም፤ ነገር ግን የክርስቶስን ትምህርት እንዳላሰናክል በሁሉ እታገሣለሁ።
እንግዲህ ይህን የመከርሁ በውኑ የሠራሁት እንደ አላዋቂ ሰው ሆኜ ነውን? ወይስ በእኔ በኩል አዎን አዎን፥ አይደለም አይደለም ማለት እንዲሆን ያን የምመክረው ለሰው ይምሰል ነውን?
ከእናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜም፥ ስቸገር ገንዘባችሁን አልተመኘሁም። ባልበቃኝም ጊዜ ወንድሞቻችን ከመቄዶንያ መጥተው አሙአሉልኝ፤ በእናንተም ላይ እንዳልከብድባችሁ በሁሉ ተጠነቀቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠነቀቃለሁ።
በዚህ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ራሳችንን የምናመሰግን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ እንደምንመካባችሁ፥ እናንተም በእኛ እንድትመኩ፥ ከልብ ሳይሆን ለሰው ይምሰል በሚመኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እንዲሆናችሁ ምክንያትን እንሰጣችኋለን።
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤