Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በእኛ ሹመት ሌላ የሚ​ቀ​ድ​መን ከሆነ የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ይህን አል​ፈ​ለ​ግ​ሁ​ትም፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ትም​ህ​ርት እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል በሁሉ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሌሎች ይህን መብት ከእናንተ ማግኘት ከቻሉ፣ እኛ ይበልጥ ማግኘት አይገባንምን? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይልቁንም ለክርስቶስ ወንጌል ዕንቅፋት እንዳንሆን ሁሉንም ነገር እንታገሣለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ፥ እኛማ ይልቁን አይኖረንም? በዚህ መብት ግን አልተጠቀምንም፥ ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል በምንም እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሌሎች ይህን ነገር ከእናንተ የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ ታዲያ፥ እኛ ከዚህ የሚበልጥ መብት እንዴት አይኖረንም? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይህን ማድረጋችንም የክርስቶስ የምሥራች ቃል ከመስፋፋት እንዳይገታ በማሰብ ሁሉን ነገር ታግሠን እንቻል ብለን ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 9:12
23 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዴን አቅ​ን​ቶ​ልኝ ሳለ አታ​ዘ​ግ​ዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።


መጥ​ተ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይወ​ጉና ያፈ​ር​ሷት ዘንድ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።


እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”


ሥራ​ቸው አንድ ስለ ነበረ ድን​ኳን ሰፊ​ዎ​ችም ስለ ነበሩ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብሮ ኖረ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይሠሩ ነበር።


ዘወ​ትር ወደ እና​ንተ ልመጣ እወ​ድድ ነበር፤ ነገር ግን ተሳ​ነኝ።


በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።


እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም?


ጌታ​ች​ንም እን​ዲሁ ወን​ጌ​ልን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ለሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው መተ​ዳ​ደ​ሪያ በዚ​ያው ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ይሆን ዘንድ አዘዘ።


እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል።


ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም መመ​ስ​ገን አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ታዝዤ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና፤ ወን​ጌ​ልን ባላ​ስ​ተ​ምር ደግሞ ወዮ​ልኝ።


እን​ግ​ዲህ ዋጋዬ ምን​ድን ነው? ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም በሹ​መቴ የማ​ገ​ኘው ሳይ​ኖር ወን​ጌ​ልን ያለ ዋጋ እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ባደ​ርግ ነው።


ለሌ​ሎች ሐዋ​ር​ያ​ቸው ባል​ሆ​ንም ለእ​ና​ን​ተስ ሐዋ​ር​ያ​ችሁ እኔ ነኝ፤ በጌ​ታ​ችን የሐ​ዋ​ር​ያ​ነቴ ማኅ​ተም እና​ንተ ናች​ሁና።


ነገር ግን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትም ቢሆን፥ የማ​ደ​ር​ገ​ውም ቢሆን፥ እነ​ርሱ እንደ እኛ የሚ​መ​ኩ​በ​ትን ያገኙ ዘንድ፥ ምክ​ን​ያት የሚ​ሹ​ትን ምክ​ን​ያት አሳ​ጣ​ቸው ዘንድ ነው።


የሚ​ገ​ዙ​አ​ች​ሁ​ንና የሚ​ቀ​ሙ​አ​ች​ሁን፥ መባያ የሚ​ያ​ደ​ር​ጓ​ች​ሁ​ንና የሚ​ታ​በ​ዩ​ባ​ች​ሁን፥ ፊታ​ች​ሁ​ንም በጥፊ የሚ​መ​ት​ዋ​ች​ሁን ትታ​ገ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁና።


ለክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ጢሮ​አዳ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩ ተከ​ፈ​ተ​ልኝ።


አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቀፍ፥ በአ​ን​ዳች ነገር ማሰ​ና​ከያ እን​ዳ​ን​ሰጥ እን​ጠ​ን​ቀቅ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos