2 ቆሮንቶስ 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ጳውሎስ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ብርቅ ግን የምደፍራችሁ በክርስቶስ የዋህነትና ቸርነት እማልዳችኋለሁ፥ በፍቅራችሁ እታመናለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ጳውሎስ፣ በእናንተ ፊት ስሆን “ዐይነ ዐፋር”፣ ከእናንተ ስርቅ ግን፣ “ደፋር” የተባልሁ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እለምናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ጳውሎስ፥ ፊት ለፊት ሳገኛችሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ርቄ ግን ደፋር የምሆንባችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እመክራችኋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ጳውሎስ በእናንተ ፊት ሳለሁ ትሑት ተባልኩ፤ ከእናንተ ስርቅ ግን በእናንተ ላይ ደፋር ተባልኩ፤ በክርስቶስ ቸርነትና ደግነት እለምናችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ራሴ ጳውሎስ፥ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ግን ብርቅ የምደፍራችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እመክራችኋለሁ፤ |
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ያነበው የነበረ የመጽሐፉ ቃልም እንዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።
እኛስ ስለ ክርስቶስ ብለን አላዋቂዎች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጠቢባን ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ፤ እናንተ ክቡራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተዋረድን ነን።
ከሰዎች መካከል “መልእክቶቹ ከባዶችና አስጨናቂዎች ናቸው፤ ሰውነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።
ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ እሠራለሁ፤ በሥጋዊ ሥርዐትም እንደምንኖር አድርገው በሚጠረጥሩን ሰዎች ላይ በድፍረት ለመናገር አስባለሁ፤ እናንተ ግን በዚህ ዓይነት ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ።
በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ፤ ማንም በክርስቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛም እንዲሁ ነንና።
እኛ እንደ ደካሞች መስለን እንደ ነበርን፥ ይህን በውርደት እናገራለሁ፤ ነገር ግን ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍራለሁ።
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
ከእርሱም ጋር አብረን እየሠራን፥ የተቀበላችኋትን የእግዚአብሔር ጸጋ ለከንቱ እንዳታደርጓት እንማልዳችኋለን።
በእናንተ ዘንድ እንዲሁ ብዙ መወደድ አለኝ፤ ስለ እናንተም የምመካበት ብዙ ነው፤ መጽናናትንም አገኘሁ፤ ከመከራዬም ሁሉ ይልቅ ደስታዬ በዛልኝ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ለተጠራሁላት አጠራር በሚገባ ትኖሩ ዘንድ በክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ እማልዳችኋለሁ።
እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም አዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ሆኜ ከተሾምሁለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቅዋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ፥
እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።