2 ዜና መዋዕል 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ወደ ኤማትሱባ ሄደ፤ በረታባትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን ወደ ሐማት ሱባ ዘመተ፤ ያዛትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ወደ ሐማት-ሱባ ሄደ አሸነፋትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን በሐማትና በጾባ ግዛቶች ላይ ዘምቶ በቊጥጥሩ ሥር አደረጋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ወደ ሐማትሱባ ሄደ፤ አሸነፋትም። |
የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ኀይሉም፥ የይሁዳ የነበረውን ደማስቆንና ሔማትን ለእስራኤል እንደ መለሰ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛቱን ለማጽናት በሄደ ጊዜ ሔማታዊውን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን መታ።