ኢዮሣፍጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተርሴስ መርከብን ሠራ፤ ነገር ግን መርከቢቱ በጋሴዎንጋቤር ተሰብራለችና አልሄደችም።
2 ዜና መዋዕል 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የዚያን ጊዜ በኤዶምያስ ምድር በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ጋሴዎንጋብርና ወደ ኤላት ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ጠረፍ ወደሚገኙት ወደ ዔጽዮንጋብርና ወደ ኤላት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም የዚያን ጊዜ በኤዶምያስ ምድር በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ዔጽዮን-ጋብርና ወደ ኤሎት ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ወደብ ወደሆኑት ወደ ዔጽዮንጋብርና ወደ ኤላት ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የዚያን ጊዜ በኤዶምያስ ምድር በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ዔጽዮን ጋብርና ወደ ኤሎት ሄደ። |
ኢዮሣፍጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተርሴስ መርከብን ሠራ፤ ነገር ግን መርከቢቱ በጋሴዎንጋቤር ተሰብራለችና አልሄደችም።
በዚያም ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን ኤላትን ወደ ሶርያ መለሰላቸው፥ አይሁድንም ከኤላት አሳደደ፤ ኤዶማውያንም ወደ ኤላት መጥተው እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይኖራሉ።
እነሆ፥ መሠረቱ ከተጣለ ጀምሮ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት እስከ ፈጸመ ድረስ ሥራው ሁሉ የተዘጋጀ ነበረ። የእግዚአብሔርም ቤት ተፈጸመ።
በሴይርም ከተቀመጡት ከወንድሞቻችን ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤሎንና ከጋስዮን-ጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።