Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 8:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኪራ​ምም መር​ከ​ቦ​ች​ንና የባ​ሕ​ርን ነገር የሚ​ያ​ው​ቁ​ትን መር​ከ​በ​ኞች በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ እጅ ላከ​ለት፤ እነ​ር​ሱም ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ አምሳ መክ​ሊት ወርቅ ወስ​ደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኪራምም ባሕሩን በሚያውቁት በራሱ መኰንኖች የሚታዘዙ መርከቦችን ላከለት፤ እነዚህም ከሰሎሞን ሰዎች ጋራ በመሆን ወደ ኦፊር ተጓዙ፤ ከዚያም አራት መቶ ዐምሳ መክሊት ወርቅ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በባርያዎቹ እጅ ላከለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን ባርያዎች ጋር ወደ ኦፊር መጡ፥ ከዚያም አራት መቶ ኀምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በባሪያዎቹ እጅ ሰደደለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን ባሪያዎች ጋር ወደ ኦፊር መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ አምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 8:18
6 Referencias Cruzadas  

ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።


የኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሴ​ፌር ለሰ​ሎ​ሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰ​ን​ደል እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕን​ቍም ደግሞ አመጡ።


በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ሰሎ​ሞን የሚ​መጣ የወ​ርቅ ሚዛን ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት መክ​ሊት ወርቅ ነበረ።


ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ተር​ሴስ የሚ​ሄዱ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በሦ​ስት በሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ ጊዜ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ወር​ቅና ብር፥ የዝ​ሆ​ንም ጥር​ስና ዝን​ጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር።


ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos