ንጉሡ ዳዊትም ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
2 ዜና መዋዕል 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ ክብሩን ይሸከም ዘንድ አይችልምና ለእርሱ ቤት ይሠራ ዘንድ ማን ይችላል? በፊቱ ዕጣን ከማጠን በቀር ቤት እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለው ሰማይ እንኳ እርሱን ይይዘው ዘንድ አይችልምና ቤተ መቅደስ ሊሠራለት የሚችል ማነው? በፊቱ ዕጣን የሚታጠንበትን እንጂ ቤተ መቅደስ እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ እርሱን ለመያዝ አይችልምና ለእርሱ ቤት መሥራት ማን ይችላል? በፊቱ ዕጣን ከማጠን በቀር ቤት ልሠራለት የምችል እኔ ማን ነኝ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ እውነቱ ከሆነ ለእግዚአብሔር በቂ የሚሆን ቤተ መቅደስን ለመሥራት የሚችል ማንም የለም፤ የሰማይና የምድር ስፋት እንኳ እግዚአብሔርን ሊይዘው አይችልም፤ ታዲያ ለእግዚአብሔር ዕጣን ለማጠን የሚበቃ ቤት ከመሥራት በቀር ለእርሱ ማደሪያ ሊሆን የሚችል ቤተ መቅደስ ለመሥራት የምሞክር እኔ ማን ነኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ ይይዘው ዘንድ አይችልምና ለእርሱ ቤት ይሠራ ዘንድ ማን ይችላል? በፊቱ ዕጣን ከማጠን በቀር ቤት እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ? |
ንጉሡ ዳዊትም ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
እርሱም ከንፍታሌም ወገን የነበረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባቱም የጢሮስ ሰው ናስ ሠራተኛ ነበረ፤ የናስንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥበብና በማስተዋል፥ በብልሃትም ተሞልቶ ነበር። ወደ ንጉሡም ወደ ሰሎሞን መጥቶ ሥራውን ሁሉ ሠራ።
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
አንተም ብዙ ሠራተኞችን፥ ድንጋይና እንጨት ወቃሪዎችንና ጠራቢዎችን፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎችን አብዝተህ ጨምር።
ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና ማስተዋልን ስጠኝ፤ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ መፍረድ የሚቻለው የለምና።”
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም ይወስንህ ዘንድ አይችልም፤ እንግዲያስ እኔ የሠራሁት ይህ ቤት ምንድን ነው?
ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን እሄድ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?
ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።
ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ ለእኔ የማይመረመረውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ አስተምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።
በዚያን ጊዜ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ከእጃችሁ ሥራ ቀዳምያቱን የተመረጠውንም መባችሁን ሁሉ፥ ለአምላካችሁም የተሳላችሁትን ሁሉ ውሰዱ።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፤ በዚያም ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሁሉ አድርግ።
ነገር ግን የተቀደሰውን ነገርህን፥ ስእለትህንም ይዘህ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙ በዚያ እንዲጠራ ወደ መረጠው ስፍራ ሂድ።