Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወ​ጣና እገባ ዘንድ ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ስጠኝ፤ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ መፍ​ረድ የሚ​ቻ​ለው የለ​ምና።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህን ሕዝብ ለመምራት እንድችል፣ ጥበብና ዕውቀትን ስጠኝ፤ አለዚያማ፣ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊያስተዳድር ይችላል?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት ለመውጣትና ለመግባት እንድችል ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህ ሕዝብህን በትክክል ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብና ዕውቀት ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብህ ላይ ይፈርድ ዘንድ የሚችል የለምና።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 1:10
14 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”


ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።


አስ​ቀ​ድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ታ​ወ​ጣና የም​ታ​ገባ አንተ ነበ​ርህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ትጠ​ብ​ቃ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ ትሆ​ና​ለህ ብሎህ” ነበር።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ኀይ​ላ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራ​ሳ​ችን እንደ ሆነ አድ​ር​ገን ምንም ልና​ስብ አይ​ገ​ባ​ንም።


በፊ​ታ​ቸው የሚ​ወ​ጣ​ው​ንና የሚ​ገ​ባ​ውን፥ የሚ​ያ​ስ​ወ​ጣ​ቸ​ው​ንና፥ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ው​ንም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር እረኛ እን​ደ​ሌ​ለው መንጋ እን​ዳ​ይ​ሆን።”


አላ​ቸ​ውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖ​ኛል፤ ከዚህ በኋላ እወ​ጣና እገባ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ርም’ ብሎ​ኛል።


የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?


ብቻ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ይስ​ጥህ፤ መን​ግ​ሥ​ት​ህ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያጽና።


ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፥ ሹማምቶችም እውነትን ይጽፋሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios