“ወንድምህን አትበድለው፤ በልብህም አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኀጢአት እንዳይሆንብህ ባልንጀራህን የምትነቅፍበትን ንገረው፤ ገሥጸውም።
1 ጢሞቴዎስ 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኀጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎች አይተው እንዲጠነቀቁ ኀጢአት የሚሠሩትን በጉባኤ ፊት ገሥጻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች እንዲፈሩ ኃጢአት የሚሠሩትን በሰዎች ሁሉ ፊት ገሥጽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሰሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው። |
“ወንድምህን አትበድለው፤ በልብህም አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኀጢአት እንዳይሆንብህ ባልንጀራህን የምትነቅፍበትን ንገረው፤ ገሥጸውም።
ይህም ነገር በኤፌሶን በሚኖሩ በአይሁድና በአረማውያን ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ ሁሉም ፈሩ፤ የጌታችን የኢየሱስንም ስም ከፍ ከፍ አደረጉ።
እነሆ፥ ያ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ያደረጋችሁት ኀዘን ምንም የማታውቁ እስከ መሆን ደርሳችሁ፥ ራሳችሁን በበጎ ሥራና በንጽሕና እስክታጸኑ ድረስ፥ ትጋትንና ክርክርን፥ ቍጣንና ፍርሀትን፥ ናፍቆትንና ቅንዐትን፥ በቀልንም አደረገላችሁ፤
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።