Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “ወን​ድ​ም​ህን አት​በ​ድ​ለው፤ በል​ብ​ህም አት​ጥ​ላው፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ት​ነ​ቅ​ፍ​በ​ትን ንገ​ረው፤ ገሥ​ጸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ ‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ የበደሉ ተካፋይ እንዳትሆን ባልንጀራህን በግልጽ ገሥጸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልነጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 19:17
23 Referencias Cruzadas  

በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።


ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ወን​ድ​ምህ አን​ተን ቢበ​ድል ብቻ​ህን ምከ​ረው፤ ቢጸ​ጸት ግን ይቅር በለው።


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።


የሥራ ፍሬ ከሌ​ላ​ቸው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ቸ​ውም ጨለማ ከሆነ ሰዎች ጋር አት​ተ​ባ​በሩ፤ ገሥ​ጹ​አ​ቸው እንጂ።


ይህን እን​ዲህ ላደ​ረገ ሞት እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እነ​ርሱ ራሳ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ እያ​ወቁ፥ እነ​ርሱ ብቻ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ያነ​ሣ​ሡ​ታል፤ ያሠ​ሩ​ታ​ልም።


ሰነፎችን አትገሥጽ እንዳይጠሉህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።


ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።


ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።


ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኀጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።


እና​ን​ተም ከዚህ ጋር ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ናችሁ፤ ይል​ቁ​ንም ይህን ያደ​ረ​ገው ከእ​ና​ንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላ​ዘ​ና​ች​ሁ​በ​ትም?


አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ “አንተ ተስ​ፋዬ ነህ፥ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር አንተ ዕድል ፋን​ታዬ ነህ” አልሁ።


ዔሳ​ውም አባቱ ስለ ባረ​ከው በያ​ዕ​ቆብ ቂም ያዘ​በት፤ ዔሳ​ውም በልቡ አለ፥ “ለአ​ባቴ የል​ቅሶ ቀን ትቅ​ረብ፤ ወን​ድ​ሜን ያዕ​ቆ​ብን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ።”


አቤ​ሴ​ሎ​ምም አም​ኖ​ንን ክፉም ሆነ መል​ካም አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም። እኅ​ቱን ትዕ​ማ​ርን ስላ​ስ​ነ​ወ​ራት አቤ​ሴ​ሎም አም​ኖ​ንን ጠል​ቶ​ታ​ልና።


ከይ​ሁ​ዳም አለ​ቆ​ችና ታላ​ላ​ቆች ጋር ተከ​ራ​ከ​ር​ሁና እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ክፉ ነገር ምን​ድን ነው? የሰ​ን​በ​ት​ንስ ቀን ታረ​ክ​ሳ​ላ​ች​ሁን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios