ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
1 ጢሞቴዎስ 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱ በሥጋ ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። |
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
ስለዚህም ነገር የሚሉትን አጥተው ሲያደንቁ ሁለት ሰዎች ከፊታቸው ቆመው ታዩአቸው፤ ልብሳቸውም ያብረቀርቅ ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
“እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።
ሁለት መላእክትንም ነጭ ልብስ ለብሰው የጌታችን የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በራስጌ፥ አንዱም በግርጌ ተቀምጠው አየች።
በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ዜናዉ ተሰማ፤ ያም መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ይኸውም የደም መሬት ማለት ነው።
አንጾኪያም በደረሱ ጊዜ ምእመናኑን ሁሉ ሰብስበው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ፥ ለአሕዛብም የሃይማኖትን በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው።
አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
አይሁዳዊንና አረማዊን አልለየም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ እግዚአብሔር ባለጸጋ ስለሆነ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና።
ነገር ግን እንዲህ እላለሁ፤ በውኑ እስራኤል ብቻ አልሰሙምን? መጽሐፍ “ነገራቸው በምድር ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ” ብሎ የለምን?
ይህም በነቢያት ቃልና የዘለዓለም ገዥ በሚሆን በእግዚአብሔር ትእዛዝ በዚህ ወራት ተገለጠ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተውና ዐውቀው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ።
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።
ስለ ሥጋ ደካማነት የኦሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተሳነው ጊዜ እግዚአብሔር በኀጢኣተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያችንም ኀጢአት በሥጋው ቀጣት።
እነርሱም አባቶቻችን ናቸው፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ ተወለደ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤ አሜን።
ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔር ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።
እኛ ማለት እኔ ጳውሎስ፥ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትና ሐሰት አይደለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያስተማርነው እውነት ነው።
እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም አዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ሆኜ ከተሾምሁለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቅዋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ፥
ዛሬ ግን እግዚአብሔር የዚህን ምክር የክብር ባለጸግነት በአሕዛብ ላይ እንዲገልጽላቸው ለፈቀደላቸው ለቅዱሳን ተገለጠላቸው፤ የምንከብርበት አለኝታችን በእናንተ አድሮ ያለ ክርስቶስ ነውና።
ይህም ወደ እናንተ የደረሰውን የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ከአያችሁበት ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያድግና ያፈራ ዘንድ ነው።
ይኸውም ልቡናቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትምህርታቸውም በማወቅ፥ በፍቅርና ፍጹምነት ባለው ባለጸግነት፥ በጥበብና በሃይማኖት፥ ስለ ክርስቶስም የሆነውን የእግዚአብሔርን ምክር በማወቅ ይጸና ዘንድ ነው።
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፤ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
መልአኩም አለኝ “የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና ዐስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።
ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤