ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፤ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ፥ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
1 ሳሙኤል 30:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤትሶር ለነበሩ፥ በራማ አዜብም ለነበሩ፥ በጌትም ለነበሩ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም፣ በቤቴል፣ በደቡብ ራሞትና በየቲር ለነበሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም፥ በቤትኤል፥ በደቡብ ራሞትና በያቲር ለነበሩ ላከላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ምርኮ በቤትኤል ለሚገኙ፥ በይሁዳ ደቡብ በራማ ለሚገኙ፥ እንዲሁም በያቲር ከተሞች ለሚገኙ ወገኖች ሁሉ ላከላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቴል ለነበሩ፥ በራሞት በደቡብ ለነበሩ፥ |
ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፤ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ፥ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
የዮሴፍም ልጆች ድንበራቸው በኢያሪኮ አንጻር በምሥራቅ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ሎዛ ትባል ወደ ነበረችው ቤቴል ይደርሳል፤
እስከ ባሌቅ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮቻቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባሜት ላይ ወደ ደቡብ ያልፋል። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዊን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይንም ሰልሉ” ብሎ ተናገራቸው፤ ሰዎቹም ወጡ፤ ጋይንም ሰለሉ።
ኢያሱም ላካቸው፤ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በባሕር በኩል ተቀመጡ፤ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።