አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ” ነበር።
1 ሳሙኤል 25:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለጌታዬ የታመነ ቤትን ይሠራለታልና፥ የጌታዬንም ጦርነት እግዚአብሔር ይዋጋለታልና የእኔን የባሪያህን ኀጢኣት፥ እባክህ፥ ይቅር በል፤ በዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታዬ የእግዚአብሔርን ጦርነት ስለሚዋጋ እግዚአብሔርም ለጌታዬ ሥርወ መንግሥቱን በርግጥ ለዘላለም የሚያጸናለት በመሆኑ፣ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዬ የጌታን ጦርነት ስለሚዋጋ ጌታም ለጌታዬ የታመነ ቤት በእርግጥ ለዘለዓለም የሚያጸናለት በመሆኑ፥ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታዬ፥ አንተ የእግዚአብሔርን ጦርነት እየተዋጋህ ነው፤ በምትኖርበትም ዘመን ሁሉ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር ማድረግን ስለማትፈልግ ስለ ፈጸምኩት በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ እግዚአብሔር አንተንና ዘሮችህን ለዘለዓለም ያነግሣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ጦርነት ስለምትዋጋ እግዚአብሔር በእውነት ለጌታዬ የታመነ ቤት ይሠራልና የእኔን የባሪያህን ኃጢአት፥ እባክህ፥ ይቅር በል፥ በዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም። |
አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ” ነበር።
በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆችን በሾምሁ ጊዜ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እንደምትሠራለት ይነግርሃል፤ እሠራለታለሁ ብለሃልና።
አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን ጆሮ ከፈትህ። አንተ፦ እኔ ቤት እሠራልሃለሁ አልህ፤ ስለዚህም ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ አሰበ።
ከእርሱም አስቀድሞ ባደረገው በአባቱ ኀጢአት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አልነበረም።
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
እኔ፦ በእስራኤል ላይ የሚገዛ ሰውን ከአንተ አላጠፋም ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።
በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ፈራጆችን ካስነሣሁበት ጊዜ ጀምሮ ጠላቶችህን ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ፤ አንተንም ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። እግዚአብሔር ደግሞ ቤትን ይሠራልሃል።
አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ በጆሮው ገልጠሃልና ስለዚህ አገልጋይህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ።
እንዲህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ! ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፦ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
በያዕቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእስራኤልም ሕማም አይታይም፤ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፤ የአለቆችም ክብር ለእርሱ ነው።
ሳሙኤልም፥ “እግዚአብሔር ከእስራኤል መንግሥትህን ዛሬ ከእጅህ ቀደዳት፤ ከአንተም ለሚሻል ለባልንጀራህ አሳልፎ ሰጣት፤
ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደለ ያውቃል። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔርም እናንተን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።”
ሳኦልም ዳዊትን፥ “ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርስዋን እድርልሃለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁንልኝ፤ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል” አለው። ሳኦልም፥ “የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን” ይል ነበር።
የታመነ ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ በልቤም፥ በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፤ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።
አቤሜሌክም መልሶ ንጉሡን፥ “ከባሪያዎቹ ሁሉ የታመነ፥ ለንጉሥም አማች የሆነ፥ የትእዛዝህ ሁሉ አለቃ፥ በቤትህም የከበረ እንደ ዳዊት ያለ ማን ነው?
እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዐይንህ አይታለች፤ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተናገሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳኦል መንገር በፈጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድምፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦልም ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች ወጣ፤ በዚያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ወደዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።
በእግሩም ላይ ወደቀች፤ እንዲህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪያህ በጆሮህ ልናገር፥ የባሪያህንም ቃል አድምጥ።
የፍልስጥኤማውያን አለቆች፥ “እነዚህ በኋላ የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አሉ፤ አንኩስም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች፥ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት ነው፤ እርሱ በእነዚህ ሁለት ዓመታት ከእኛ ጋር ነበረ፤ ወደ እኔም ከተጠጋበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አላገኘሁበትም” አላቸው።
ዳዊትም ወደ ሴቄላቅ በመጣ ጊዜ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ” ብሎ ከምርኮው ላከላቸው።