በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
1 ሳሙኤል 20:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም፥ “እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይፈልገው” ብሎ ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዮናታን፣ “የዳዊትን ጠላቶች እግዚአብሔር ይፋረዳቸው” በማለት ከዳዊት ቤት ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዮናታን፥ “የዳዊትን ጠላቶች ጌታ ይፋረዳቸው” በማለት ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ የገባነው ቃል ኪዳን ለዘለቄታው እንደ ተጠበቀ ይኑር፤ ይህን ቃል ኪዳን ብታፈርስ ግን እግዚአብሔር ይፈርድብሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም፦ እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይፈልገው ብሎ ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። |
በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤
ንጉሡም ለሳኦል የወለደቻቸውን የኢዮሄልን ልጅ የሩጻፋን ሁለቱን ልጆች ሄርሞንስቴንና ሜምፌቡስቴን፥ ለመሓላታዊውም ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድራ የወለደቻቸውን የሳኦልን ልጅ የሜሮብን አምስቱን ልጆች ወሰደ፤
የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፤ በምድር ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኀጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘግይ።
አምላካችንን እግዚአብሔርን እንድንክደው፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህልን ቍርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይመራመረን፤
ዮናታንም ዳዊትን፥ “በሰላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ምስክር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል” አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።
ሁላችሁ በላዬ ዶልታችሁ ተነሣችሁብኝ፤ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ሲማማል ማንም አልገለጠልኝም፤ ከእናንተም አንድ ለእኔ የሚያዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገልጋዬን እንዲዶልት ሲያስነሣብኝ ማንም አላስታወቀኝም” አላቸው።
ለናባልም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ብንተው፥ እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ፤ እንዲህም ይጨምር” ብሎ ነበር።
አሁንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እንዳትገባና፥ እጅህን እንድታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን ተከትለው አገኙአቸው። ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን፥ ሜልኪሳንም ገደሉአቸው።