Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ሳሙኤል 31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የሳ​ኦ​ልና የል​ጆቹ ሞት

1 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።

2 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሳኦ​ል​ንና ልጆ​ቹን ተከ​ት​ለው አገ​ኙ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የሳ​ኦ​ልን ልጆች ዮና​ታ​ን​ንና አሚ​ና​ዳ​ብን፥ ሜል​ኪ​ሳ​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።

3 ሰል​ፍም በሳ​ኦል ላይ ጠነ​ከረ፤ ቀስ​ተ​ኞ​ችም አገ​ኙት፤ ታፋ​ው​ንም ወጉት።

4 ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ወ​ጉ​ኝና እን​ዳ​ይ​ሳ​ለ​ቁ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።

5 ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰ​ይፉ ላይ ወደቀ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሞተ።

6 በዚ​ያም ቀን ሳኦል ሦስ​ቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በአ​ንድ ላይ ሞቱ።

7 በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።

8 በማ​ግ​ሥ​ቱም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ልና ሦስቱ ልጆቹ በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።

9 አገ​ላ​ብ​ጠ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ገፈፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ላሉ ለጣ​ዖ​ታ​ቱና ለሕ​ዝቡ የም​ሥ​ራች ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሁሉ ላኩ።

10 የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም በአ​ስ​ታ​ሮት መቅ​ደስ ውስጥ አኖ​ሩት። ሬሳ​ው​ንም በቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉት።

11 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በሳ​ኦል ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሰዎች በሰሙ ጊዜ፥ ጀግ​ኖች ሰዎች ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ሌሊ​ቱን ሁሉ ሄዱ፥

12 የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።

13 አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰዱ፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ባለው የእ​ርሻ ቦታ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos