Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 20:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህ ዮናታን፥ “የዳዊትን ጠላቶች ጌታ ይፋረዳቸው” በማለት ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ ዮናታን፣ “የዳዊትን ጠላቶች እግዚአብሔር ይፋረዳቸው” በማለት ከዳዊት ቤት ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህ የገባነው ቃል ኪዳን ለዘለቄታው እንደ ተጠበቀ ይኑር፤ ይህን ቃል ኪዳን ብታፈርስ ግን እግዚአብሔር ይፈርድብሃል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ዮናታንም፦ እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይፈልገው ብሎ ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 20:16
13 Referencias Cruzadas  

በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥


ነገር ግን ንጉሡ የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን፤ የሳኦል ልጅ ሜራብ ለመሖላታዊው ለባርዚላይ ልጅ ለአድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤


የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ለከለዳውያን ለማገልገል አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፥ መልካምም ይሆንላችኋል።


ለእግዚአብሔር ለጌታ ስእለት በተሳልህ ጊዜ እግዚአብሔር ጌታ ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና ከመክፈል አታዘገይ።


ጌታን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የአንድነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደሆነ ጌታ እርሱ ራሱ ይበቀለን፤


ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤


ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።


በእኔ ላይ የዶለታችሁት ለዚህ ነውን? ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ሲያደርግ ማንም አልነገረኝም፤ ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ፥ ልጄ አገልጋዬን በእኔ ላይ እንዲያደባብኝ ማነሣሣቱን ከእናንተ ስለ እኔ ተቆርቆሮ የነገረኝ ማንም የለም።”


ሁለቱም በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ከዚያም ዮናታን ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊት ግን እዚያው ሖሬሽ ተቀመጠ።


ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳ በሕይወት ባስቀር እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያድርግበት፥ ከዚህም የከፋ ይጨምርበት!”


ጌታዬ ሆይ፤ በሕያው ጌታ፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ ጌታ ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤


ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን አጥብቀው ተከታተሉ፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፥ አቢናዳብንና ማልኪሹዓን ገደሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos