ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
1 ሳሙኤል 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ፥ እኔም ባላስታውቅህ፥ በሰላምም ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ፤ ይህንም ይጨምር፤ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፣ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፣ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። እግዚአብሔር ከአባቴ ጋራ እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋራ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፥ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፥ ጌታ ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። ጌታ ከአባቴ ጋር እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋር ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተን ለመጒዳት የሚፈልግ ከሆነ ግን፥ ስለ እርሱ ባልገልጥልህና አንተም በሰላም እንድታመልጥ ባላደርግ አባቴ በአንተ ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ክፉ ነገር እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያድርሰው። እግዚአብሔር ከአባቴ ጋር እንደ ነበር ከአንተም ጋር ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ እኔም ባላስታውቅህ በደህና ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ ይህንም ይጨምር፥ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን። |
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋብዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳትጠልቅ እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ” ብሎ ማለ።
እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሥ ጋር እንደ ነበረ እንዲሁ ከሰሎሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሡ ከዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርግ።”
ኤልዛቤልም፥ “አንተ ኤልያስ ከሆንህ እኔም ኤልዛቤል ከሆንሁ ነገ በዚህ ጊዜ ሰውነትህን ከእነዚህ እንደ አንዱ ሰውነት ባላደርጋት፥ አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ” ብላ ወደ ኤልያስ ላከች።
ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም በፊቱ አስቀምጡና፦ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው ይመስክሩበት፤ አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መትታችሁ ግደሉት።”
አሁንም ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም እንደ ተናገረው ያከናውንልህ፤ የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ።
ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፥ የሰማችሁትንና ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከሁላችሁ ጋር ይሆናል።
በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የሚቋቋምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ ቸልም አልልህም።
በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።
ዳዊትም፥ “ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል” አለ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን” አለው።
እኔም እወጣለሁ፤ አንተም ባለህበት እርሻ በአባቴ አጠገብ እቆማለሁ፤ ስለ አንተም ለአባቴ እነግረዋለሁ፤ የሆነውንም አይቼ እነግርሃለሁ” ብሎ ለዳዊት ነገረው።
ዮናታንም ዳዊትን አለው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ በዚህ ጊዜ አባቴን መርምሬ እነሆ፥ በዳዊት ላይ መልካም ቢያስብ፥ እነሆ፥ ወደ ሜዳ ወደ አንተ አልልክም፤ ይህም ምልክት ይሁንህ፤
ለናባልም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ብንተው፥ እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ፤ እንዲህም ይጨምር” ብሎ ነበር።
እርሱም፥ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? ከእኔ አትሸሽግ፤ ከነገረህና ከሰማኸው ነገር ሁሉ የሸሸግኸኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፤ እንዲህም ይጨምርብህ” አለው።