1 ሳሙኤል 15:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም አጋግን፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልጌላ ወጋው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም፣ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፣ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቈራረጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በጌታ ፊት ቆራረጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ ሳሙኤል “የአንተ ሰይፍ ብዙዎች እናቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ የአንተም እናት ልጅ አልባ ሆና ትቀራለች” አለው። ከዚህም በኋላ በጌልገላ በሚገኘው በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት አጋግን ቈራርጦ ጣለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው። |
ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር ፤ እጁንም በአወረደ ጊዜ ዐማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፤ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፤ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፤ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፤ ጐልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፤ መትተዋቸውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳደዱአቸው። ወደ ከተማም ተመለሱ።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”
ሳሙኤልም፥ “የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?” አለ።