እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
1 ነገሥት 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮቼ ከሊባኖስ ወደ ባሕር ያወርዱልሃል፤ እኔም በመርከብ አድርጌ በባሕር ላይ እያንሳፈፍሁ አንተ እስከ ወሰንኸው ስፍራ ድረስ አደርስልሃለሁ፤ በዚያም እፈታዋለሁ፤ አንተም ከዚያ ታስወስደዋለህ፤ አንተም ፈቃዴን ታደርጋለህ፤ ለቤተ ሰቦቼም ቀለብ የሚሆነውን ትሰጠኛለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቼ ግንዱን ከሊባኖስ እስከ ባሕሩ ድረስ ጐትተው ያወርዳሉ፤ እኔም ግንዱ ሁሉ ታስሮ አንተ እስከ ወሰንኸው ስፍራ በባሕር ተንሳፍፎ እንዲደርስ አደርጋለሁ፤ እዚያም እኔ እፈታዋለሁ፤ አንተም ትወስደዋለህ፤ አንተም ለቤተ ሰቤ ቀለብ በመስጠት ፍላጎቴን ታሟላለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእኔ ሰዎችም ግንዶቹን ከሊባኖስ ወደ ባሕር ያወርዳሉ፤ አንድነት ጠፍረው አስረውም አንተ ወደምትመርጠው ጠረፍ ተንሳፍፈው እንዲደርሱ ያደርጋሉ፤ በዚያም የእኔ ሰዎች ማሰሪያውን ፈተው ለአንተ ሰዎች ያስረክቡአቸዋል፤ አንተም በበኩልህ በቤተ መንግሥቴ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ምግብ በመላክ ፍላጎቴን ታረካለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ ሰዎችም ግንዶቹን ከሊባኖስ ወደ ባሕር ያወርዳሉ፤ አንድነት ጠፍረው አስረውም አንተ ወደምትመርጠው ጠረፍ ተንሳፍፈው እንዲደርሱ ያደርጋሉ፤ በዚያም የእኔ ሰዎች ማሰሪያውን ፈተው ለአንተ ሰዎች ያስረክቡአቸዋል፤ አንተም በበኩልህ በቤተ መንግሥቴ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ምግብ በመላክ ፍላጎቴን ታረካለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቼ ከሊባኖስ ወደ ባሕር ይጐትቱታል፤ እኔም በታንኳ አድርጌ በባሕር ላይ እያንሳፈፍሁ አንተ እስከ ወሰንኸው ስፍራ ድረስ አደርስልሃለሁ፤ በዚያም እፈታዋለሁ፥ አንተም ከዚያ ታስወስደዋለህ፤ አንተም ፈቃዴን ታደርጋለህ፤ ለቤቴም ቀለብ የሚሆነውን ትሰጠኛለህ፤” ብሎ ወደ ሰሎሞን ላከ። |
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
ኪራምም እንዲህ ሲል ወደ ሰሎሞን ላከ፥ “የላክህብኝን ሁሉ ሰማሁ፤ ስለ ዝግባውና ስለ ጥዱ እንጨት ፈቃድህን ሁሉ አደርጋለሁ።
ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ባሕሩን መቅዘፍ የሚያውቁ መርከበኞች አገልጋዮቹን ላከ።
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን፥ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባንም እንጨት በብዛት በቆላ እንደሚገኝ ሾላ በይሁዳ አኖረ።
እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንልካለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ብር ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ በባሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎች መብልና መጠጥ፥ ዘይትም ሰጡ።
እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ላይ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አበዛሁ፤ ልቤንም ለጥበብና ለዕውቀት ሰጠሁ፥” በማለት ተናገርሁ።
ይሁዳና እስራኤል ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ስንዴንም ይሸምቱልሽ ነበር፤ ሰሊሆትንና በለሶንን፥ ዘይትንና የተወደደ ማርን፥ ርጢንንም ከአንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።
ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ተቈጥቶ ነበር፤ በአንድነትም ወደ እርሱ መጥተው የንጉሡን ቢትወደድ በላስጦስን እንዲያስታርቃቸው ማለዱት፤ የሀገራቸው ምግብ ከንጉሥ ሄርድስ ነበርና።
እኔ እንድሻገርና፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር፥ ያንም መልካሙን ተራራማውን ሀገር አንጢ ሊባኖስንም እንዳይ ፍቀድልኝ።