Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ጥበ​ብን አበ​ዛሁ፤ ልቤ​ንም ለጥ​በ​ብና ለዕ​ው​ቀት ሰጠሁ፥” በማ​ለት ተና​ገ​ርሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኔም በልቤ፣ “እነሆ፤ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከገዙት ከማንኛቸውም ይልቅ ታላቅ ሆኛለሁ፤ ጥበብም በዝቶልኛል፤ በብዙ ጥበብና ዕውቀት ተመክሮም ዐልፌአለሁ” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እኔ በልቤ፦ እነሆ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ላይ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አብዝቼ ጨመርሁ፥ ልቤም ብዙ ጥበብንና እውቀትን ተመለከተ ብዬ ተናገርሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔማ በልቤ “ከእኔ በፊት ኢየሩሳሌምን ከገዙት ሁሉ ይበልጥ ታላቅና የጥበብ ሰው ሆኛለሁ፤ የጥበብንና የዕውቀትን ምንነት መርምሬ አጥንቻለሁ” ብዬ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እኔ በልቤ፦ እነሆ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ላይ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አብዝቼ ጨመርሁ፥ ልቤም ብዙ ጥበብንና እውቀትን ተመለከተ ብዬ ተናገርሁ።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 1:16
20 Referencias Cruzadas  

እኔም መጥቼ በዐ​ይኔ እስ​ካይ ድረስ የነ​ገ​ሩ​ኝን አላ​መ​ን​ሁም ነበር ፤ እነ​ሆም፥ እኩ​ሌ​ታ​ውን አል​ነ​ገ​ሩ​ኝም ነበር፤ በሀ​ገሬ ሳለሁ ከነ​ገ​ሩኝ ይልቅ የበ​ለጠ መል​ካም ተጨ​ማሪ አየሁ።


የሰ​ሎ​ሞ​ንም ጥበብ ከቀ​ደሙ ሰዎች ሁሉ ጥበ​ብና ከግ​ብፅ ጥበብ ሁሉ በዛ።


አገ​ል​ጋ​ዮቼ ከሊ​ባ​ኖስ ወደ ባሕር ያወ​ር​ዱ​ል​ሃል፤ እኔም በመ​ር​ከብ አድ​ርጌ በባ​ሕር ላይ እያ​ን​ሳ​ፈ​ፍሁ አንተ እስከ ወሰ​ን​ኸው ስፍራ ድረስ አደ​ር​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ በዚ​ያም እፈ​ታ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ከዚያ ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አን​ተም ፈቃ​ዴን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ለቤተ ሰቦ​ቼም ቀለብ የሚ​ሆ​ነ​ውን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።”


የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶር​ያ​ዊ​ውን ይህን ንዕ​ማ​ንን ማረው፤ ካመ​ጣ​ለ​ትም ነገር ምንም አል​ተ​ቀ​በ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በስ​ተ​ኋ​ላው እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች እወ​ስ​ዳ​ለሁ” አለ።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም ደግሞ አለ፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ቤት ይሠራ ዘንድ ጥበ​በ​ኛና ብል​ሃ​ተኛ፥ አስ​ተ​ዋ​ይም ልጅ ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት የሰጠ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የፈ​ጠረ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን።


ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።


የሚ​መጣ ትው​ልድ የሚ​ወ​ለ​ዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነ​ሥ​ተ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ቸው ይነ​ግ​ራሉ።


እኔ በልቤ፥ “ና በደ​ስ​ታም እፈ​ት​ን​ሃ​ለሁ፥ እነሆ፥ መል​ካ​ም​ንም እይ” አልሁ፤ ይህም እነሆ፥ ከንቱ ነበረ።


እኔም በልቤ፥ “አላ​ዋ​ቂን የሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲሁ እኔ​ንም ያገ​ኘ​ኛል፤ እኔም ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ?” አልሁ፤ የዚ​ያን ጊዜም በልቤ፥ “ይህ ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ፥ አላ​ዋቂ በከ​ንቱ መና​ገ​ርን ያበ​ዛ​ልና።


ከእ​ኔም አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ከበ​ርሁ፥ ታላ​ቅም ሆንሁ። ጥበ​ቤም ከእኔ ጋር ጸና​ች​ልኝ።


እኔም በልቤ፥ “በዚያ ለነ​ገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለ​ውና በጻ​ድ​ቁና በኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ዳል” አልሁ።


“ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትል​ቅም ሰገ​ነት እሠ​ራ​ለሁ ለሚል፥ መስ​ኮ​ት​ንም ለሚ​ያ​ወጣ፥ በዝ​ግ​ባም ሥራ ለሚ​ያ​ስ​ጌጥ፥ በቀይ ቀለ​ምም ለሚ​ቀ​ባው ወዮ​ለት፤


ጠን​ካራ ምግብ ግን መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ዉን ለመ​ለ​የት በሥ​ራ​ቸው የለ​መደ ልቡና ላላ​ቸው ለፍ​ጹ​ማን ሰዎች ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos