Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ትና በጥ​በብ በለጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ንጉሥ ሰሎሞን በሀብትም ሆነ በጥበብ ከምድር ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ንጉሡም ሰሎሞን ከምድር ነገሥታት ሁሉ በሀብትና በጥበብ በለጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ንጉሥ ሰሎሞን በዓለም ከሚገኝ ከማንኛውም ንጉሥ ይበልጥ ሀብታምና ጥበበኛ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ንጉሡም ሰሎሞን ከምድር ነገሥታት ሁሉ በባለጠግነትና በጥበብ በለጠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:22
10 Referencias Cruzadas  

ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። ካንተ በፊት ለነ​በሩ ነገ​ሥ​ታት ያል​ተ​ሰ​ጠ​ውን፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለሚ​ነሡ የማ​ይ​ሰ​ጠ​ውን ብል​ፅ​ግ​ናን፥ ገን​ዘ​ብ​ንና ክብ​ርን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።


የም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ውን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።


አገ​ል​ጋ​ዮቼ ከሊ​ባ​ኖስ ወደ ባሕር ያወ​ር​ዱ​ል​ሃል፤ እኔም በመ​ር​ከብ አድ​ርጌ በባ​ሕር ላይ እያ​ን​ሳ​ፈ​ፍሁ አንተ እስከ ወሰ​ን​ኸው ስፍራ ድረስ አደ​ር​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ በዚ​ያም እፈ​ታ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ከዚያ ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አን​ተም ፈቃ​ዴን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ለቤተ ሰቦ​ቼም ቀለብ የሚ​ሆ​ነ​ውን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።”


ሰሎ​ሞ​ንም ለኪ​ራም ስለ ቤቱ ቀለብ ሃያ ሺህ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ ሃያ ሺህም በቤት መስ​ፈ​ሪያ ጥሩ ዘይት ይሰ​ጠው ነበር፤ ሰሎ​ሞ​ንም ለኪ​ራም በየ​ዓ​መቱ ይህን ይሰጥ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios