1 ነገሥት 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን የግብጽ ንጉሥ የፈርዖን ወዳጅ ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ። እርሱም ቤተ መንግሥቱን፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጥር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አስቀመጣት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን የግብጽን ንጉሥ ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ፤ እርሷንም አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፥ የጌታን ቤትና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጽር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን የግብጽን ንጉሥ ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ፤ እርስዋንም አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፥ ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ዙሪያ ቅጽር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንን ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አመጣት። |
ንጉሡም ሰሎሞን ሴቶችን ይወድ ነበር፥ ከባዕዳን ሕዝብም የፈርዖንን ልጅ፥ ሞዓባውያትንና አሞናውያትን፥ ሶርያውያትንና ሲዶናውያትን፥ ኤዶማውያትንና አሞሬዎናውያትንም፥ ኬጤዎናውያትንም፦ ሚስቶችን አገባ።
የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ አራት ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
ከፍርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌላውም አደባባይ ውስጥ የነበረውን የሚኖርበትን ቤት እንዲሁ ሠራ፤ እንደዚህም ቤት ያለ ቤትን ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ሠራ።
ከዚህም በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን ያደርገው ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥
ሰሎሞንም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት።
እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽሞላቸው የነበረውን ቤት እንሠራለን።
ትእዛዝህን እናፈርስ ዘንድ ተመልሰናልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚሠሩ ከእነዚህ አሕዛብ ጋርም ተጋብተናልና ከእኛ ከሞት የሚያመልጥ እስከማይኖር ድረስ ፈጽመህ አትቈጣን።