Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ነበ​ረው፤ ከአ​ክ​ዓ​ብም ወገን ሚስት አገባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢዮሣፍጥ ታላቅ ሀብትና ክብር ባገኘ ጊዜ፣ ከአክዓብ ጋራ በጋብቻ ተሳሰረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለኢዮሣፍጥም ብዙ ሀብትና ክብር ነበረው፤ እርሱም ከአክዓብ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ ትስስርን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በሀብት በበለጸገና ዝነኛ በሆነ ጊዜ የእርሱና የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቤተሰብ በጋብቻ እንዲተሳሰሩ አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለኢዮሳፍጥም ብዙ ብልጥግናና ክብር ነበረው፤ ለአክዓብም ጋብቻ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 18:1
17 Referencias Cruzadas  

ሌሎች ሠራ​ዊ​ትን እና​መ​ጣ​ል​ሃ​ለን፤ አን​ተም ቀድሞ በሞ​ቱ​ብህ ሠራ​ዊት ምትክ ሹም፤ ፈረ​ሱን በፈ​ረስ ፋንታ፥ ሰረ​ገ​ላ​ውን በሰ​ረ​ገላ ፋንታ ለውጥ፤ በሜ​ዳ​ውም እን​ዋ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፤ ድልም እና​ደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለን።” እር​ሱም ምክ​ራ​ቸ​ውን ሰማ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


በሰ​ማ​ር​ያም ሦስት ዓመት ተቀ​መጠ፤ በሶ​ር​ያና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እየ​በ​ረ​ታና እጅ​ግም እየ​ከ​በረ ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ግን​ቦ​ች​ንና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን ሠራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ቱን በእጁ አጸና፤ ይሁ​ዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ አመጣ፤ እጅ​ግም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ሆነ​ለት።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


ከዚ​ህም በኋላ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​በረ፤ ይህም በደ​ልን የሠራ ነበር፦


የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


ተጠ​ራ​ጣ​ሪ​ዎች አት​ሁኑ፤ ወደ​ማ​ያ​ምኑ ሰዎች አን​ድ​ነ​ትም አት​ሂዱ፤ ጽድ​ቅን ከኀ​ጢ​አት ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ማን ነው? ብር​ሃ​ን​ንስ ከጨ​ለማ ጋር የሚ​ቀ​ላ​ቅል ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos