ሰሎሞንም ልዩ ከሆኑ ከአሕዝብ ለአገባቸው ሚስቶቹ ሁሉ እንዲህ አደረገ፤ ለጣዖቶቻቸውም መሥዋዕትን ሠዋ፤ ዕጣንም አጠነ።
1 ነገሥት 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሰሎሞን ሴቶችን ይወድ ነበር፥ ከባዕዳን ሕዝብም የፈርዖንን ልጅ፥ ሞዓባውያትንና አሞናውያትን፥ ሶርያውያትንና ሲዶናውያትን፥ ኤዶማውያትንና አሞሬዎናውያትንም፥ ኬጤዎናውያትንም፦ ሚስቶችን አገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን ማለትም ሞዓባውያትን፣ አሞናውያትን፣ ኤዶማውያትን፣ ሲዶናውያትን፣ ኬጢያውያትን አፈቀረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ በዚህም መሠረት ከግብጽ ንጉሥ ልጅ ሌላ የሒታውያን፥ የሞዓባውያን፥ የዐሞናውያን፥ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ በዚህም መሠረት ከግብጽ ንጉሥ ልጅ ሌላ የሒታውያን፥ የሞአባውያን፥ የዐሞናውያን፥ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ፥ በሞዓባውያንና በአሞናውያን በኤዶማውያንም በሲዶናውያንና በሒታውያን ሴቶች፥ በብዙ እንግዶች ሴቶች ፍቅር ተነደፈ። |
ሰሎሞንም ልዩ ከሆኑ ከአሕዝብ ለአገባቸው ሚስቶቹ ሁሉ እንዲህ አደረገ፤ ለጣዖቶቻቸውም መሥዋዕትን ሠዋ፤ ዕጣንም አጠነ።
የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ነገሠ፤ ሮብዓምም ንጉሥ በሆነ ጊዜ የአርባ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ስሙን ያኖርባት ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም ናዕማ ነበረ፥ እርስዋም አሞናዊት ነበረች።
በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ አልበቃውም፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤያትባሔልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በዓልን አመለከ ሰገደለትም።
ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት።
ይህም ከተፈጸመ በኋላ የሕዝቡ አለቆች ወደ እኔ ቀርበው፥ “የእስራኤል ሕዝብ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ እንደ ከነዓናውያን፥ እንደ ኬጤዎናውያን፥ እንደ ፌርዜዎናውያን፦ እንደ ኢያቡሴዎናውያን፥ እንደ አሞናውያን፥ እንደ ሞዓባውያን፥ እንደ ግብፃውያንና እንደ አሞራውያን ርኵሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር አሕዛብ አልተለዩም፤
ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹሞቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ።
ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።
ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤
የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።