1 ቆሮንቶስ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍጹማንም እንድትሆኑ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስንም መምጣት ተስፋ አድርጋችሁ ፍጹም ጸጋን እንዳታጡ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጕጕት በመጠባበቅ ላይ ሳላችሁ፣ ማንኛውም መንፈሳዊ ስጦታ አይጐድልባችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ፥ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በመጠባበቅ ስትኖሩ ምንም ዐይነት መንፈሳዊ ስጦታ አይጐድልባችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤ |
እናንተም፥ በመጣና በር በመታ ጊዜ ወዲያው ይከፍቱለት ዘንድ ከሰርግ እስኪመለስ ጌታቸውን እንደሚጠብቁ ሰዎች ሁኑ።
ነገር ግን የሚተክዝ ዓለም ብቻ አይደለም፤ የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ የተቀበልነው እናም ደግሞ እናዝናለን እንጂ፤ የነፍሳችንን ድኅነት እናገኝ ዘንድ የልጅነትን ክብር ተስፋ እናደርጋለንና፤ በእምነትም ድነናልና።
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
እከብድባችሁ ዘንድ ወደ እናንተ ካለመምጣቴ በቀር፥ ከአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያሳነስኋችሁ በምንድን ነው? ይህቺን በደሌን ይቅር በሉኝ።
እኛስ ሀገራችን በሰማይ ያለችው ናት፤ ከዚያም እርሱን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።
ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።