ዘፍጥረት 32:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፣ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦታ ስም መሃናይም አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፥ “እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው!” አለ። የዚያንም ስፍራ ስም ማሃናይም ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባያቸውም ጊዜ “እግዚአብሔር ከሠራዊቱ ጋር የሚሠፍርበት ቦታ ነው” አለ፤ ስለዚህ ያንን ቦታ ማሕናይም ብሎ ጠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም በአያቸው ጊዜ፥ “እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው” አለ፤ የዚያንም ስፍራ ስም “ተዓይን” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፦ እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው አለ የዚያንም ስፍራ ስም መሃናይም ብሎ ጠራው። |
“ወደ መሃናይም በሄድሁ ጊዜ፣ ክፉኛ የረገመኝ የባሑሪም ሰው የብንያማዊው የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ፤ ከአንተ ዘንድ ይገኛል፤ ሊቀበለኝ ወደ ዮርዳኖስ ሲወርድ፣ ‘በሰይፍ አልገድልህም’ ብዬ በእግዚአብሔር ስም ምዬለታለሁ፤
ኤልሳዕም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ያይ ዘንድ እባክህ ዐይኖቹን ክፈትለት” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የአገልጋዩን ዐይኖች ከፈተለት፤ ሲመለከትም፤ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፤ ተመለሺ፤ ኧረ ተመለሺ፤ እንድናይሽ ተመለሺ፤ እባክሽ ተመለሺ። የመሃናይምን ዘፈን እንደሚመለከት ሰው፣ ሱላማጢስን የምትመለከቷት ለምንድን ነው?
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ለምን ወደ አንተ እንደ መጣሁ ታውቃለህ? የፋርስን አለቃ ለመውጋት በቶሎ እመለሳለሁ፤ እኔም ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል።
እርሱም፣ “አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ በመሆኔ እነሆ፤ መጥቻለሁ” ሲል መለሰለት፤ ኢያሱም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፣ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው።