ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
ሶፎንያስ 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጣራ ላይ ወጥተው ለፀሐይ፥ ለጨረቃና ለከዋክብት የሚሰግዱትን አጠፋለሁ፤ እኔን እያመለኩና በስሜ እየማሉ፥ ዘወር ብለው ደግሞ ሚልኮም ተብሎ በሚጠራው ጣዖት ስም የሚምሉትን እደመስሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣ በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣ ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣ በሚልኮምም ደግሞ የሚምሉትን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰገነትም ላይ ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ ለጌታ የሚሰግዱትንና በእርሱም የሚምሉትን፥ በንጉሣቸውም ደግሞ የሚምሉትን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥ |
ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር። ከእያንዳንዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፤
በዚህም ዐይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክታቸው ይሰግዱ ነበር።
እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዐይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው።
ንጉሥ አካዝ ባሠራቸው መኖሪያ ክፍሎች ጣራ ላይ በሚገኘው ቤተ መንግሥት የይሁዳ ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን መሠዊያዎችና በቤተ መቅደሱ ሁለት አደባባዮች ንጉሥ ምናሴ አሠርቶአቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ኢዮስያስ ደመሰሳቸው፤ መሠዊያዎቹንም አንከታክቶ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ ጣላቸው።
“አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።”
በእስራኤል ስም የምትጠሩ፥ ከይሁዳ ወገን የሆናችሁ፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች! ይህን ስሙ። እናንተ በታማኝነትና በእውነት ሳይሆን፥ የእስራኤልን አምላክ እናመልካለን ትላላችሁ፤ በእግዚአብሔር ስምም ትምላላችሁ።
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
የኢየሩሳሌም ሕዝብና የይሁዳ ነገሥታት የሚኖሩባቸው ቤቶች፥ እንዲሁም በጣራዎቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ዕጣን የሚታጠንባቸውና ለባዕዳን አማልክትም የወይን ጠጅ የሚፈስባቸው ቤቶች ሁሉ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።”
ይህችን ከተማ የከበቡ ባቢሎናውያን መጥተው ያቃጥሉአታል፤ እንደዚሁም እኔን ለማስቈጣት በጣራዎቻቸው ላይ ለባዓል ጣዖት ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትንና ለሌሎችም ጣዖቶች የመጠጥ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን ቤቶች ያቃጥላሉ።
እግዚአብሔር ስለ ዐሞን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትምን? ወራሾች የሉትምን? ታዲያ ሚልኮም የተባለውን ጣዖት የሚያመልኩ ወገኖች የጋድን ነገድ አስለቅቀው በከተሞቹ የሰፈሩት ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን ትተው ሐሰተኞች አማልክትን ያመልካሉ፤ ታዲያ እኔ የእነርሱን ኃጢአት ይቅር የምለው ለምንድን ነው? እኔ ለሕዝቤ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ሁሉ በመስጠት እንዲጠግቡ አደረግሁ፤ እነርሱ ግን አመንዝሮች ሆኑ፤ ማደሪያቸውም በአመንዝሮች ቤት ሆነ።
ከዚህም የተነሣ ትሰርቃላችሁ፤ ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ ምላችሁም በሐሰት ትመሰክራላችሁ፤ ለባዓል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከዚህ በፊት የማታውቁአቸውን አማልክት ታመልካላችሁ።
ዐፅሞቻቸው ተሰብስበው በመቀበር ፈንታ፥ እንደ ጒድፍ የትም ይጣላሉ፤ እነርሱም፥ ሕዝቡ በማምለክና ምክር በመጠየቅ በፍቅር ያገለግሉአቸው በነበሩት በፀሐይ፥ በጨረቃና በከዋክብት ፊት ይበተናሉ።
ልባቸው በተንኰል የተሞላ ነው፤ የበደላቸውንም ዋጋ ያገኛሉ፤ እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ሁሉ ይሰባብራል፤ የጣዖት መስገጃ ዐምዶቻቸውንም ያፈራርሳል።
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እናንተ ብታመነዝሩም እንኳ የይሁዳ ሕዝብ በደለኛ እንዲሆን አታድርጉ፤ ወደ ጌልጌላ ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።
“አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፤ ወይም አንዱን ይጠላል፥ ሌላውንም ይወዳል፤ ወይም አንዱን ያከብራል፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ አገልጋይ መሆን አይችልም።
ምክንያቱም፦ “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤ ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል።
በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።
በመካከላችሁ ከቀሩት ሕዝቦች ጋር ከቶ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፤ በእነርሱም አትማሉ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች አትሁኑ፤ አትስገዱላቸውም።