ዘካርያስ 2:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ መጥቼ በመካከላችሁ ስለምኖር የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ዘምሩ! ደስም ይበላችሁ!” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ ደስም ይበልሽ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሡ! ተነሡ! ከሰሜን ምድር ሽሹ፥ ይላል ጌታ፤ እንደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ ደስም ይበልሽ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ ደስም ይበልሽ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
ስለ እርሱም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፥ ‘ሰናክሬም ሆይ! የኢየሩሳሌም ሕዝብ አንተን በመናቅ ያፌዙብሃል፤ በምትሸሽበትም ጊዜ ከበስተኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
እንግዲህ ከባቢሎን ወጥታችሁ ሽሹ፤ “እግዚአብሔር አገልጋዩን እስራኤልን አድኖአል” የሚለውን የምሥራች ቃል በደስታ አብሥሩ፤ በየስፍራውም እንዲታወቅ አድርጉ።
ስለዚህ አንተ እግዚአብሔር የተቤዠኻቸው እየዘመሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፤ ዘላቂ ደስታንም እንደ ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ሐሴትና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ግን ከእነርሱ ይወገዳል።
እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባል ካላት ሴት ይልቅ ፈት የሆነችው ልጆች ብዛት ያላቸው ስለ ሆነ፥ ልጅ እንዳልወለደችና አምጣ እንደማታውቀው ሴት የሆንሽው ኢየሩሳሌም ሆይ! እልል እያልሽ ዘምሪ!
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
ይህም ሲፈጸም በምታዩበት ጊዜ ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ ሰውነታችሁም እንደ ሣር ይለመልማል፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከአገልጋዮቹ ጋር፥ ቊጣው ግን በሚጠሉት ላይ እንደሚሆን ይታወቃል።”
በዚያም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ፤ በደስታም እልል ይላሉ፤ አበዛቸዋለሁ እንጂ ቊጥራቸው አይቀንስም፤ ክብር እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አይናቁም።
ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።
በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
በአራቱም አቅጣጫ ያሉት የከተማይቱ የቅጽር ግንቦች ጠቅላላ ርዝመት ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ከአሁን በኋላ የከተማይቱ መጠሪያ ስም “እግዚአብሔር በዚያ አለ!” የሚል ይሆናል።
እግዚአብሔር አምላክሽ ከአንቺ ጋር ነው፤ በኀይሉም ድልን ያጐናጽፍሻል፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያድስሻል፤ ሕዝቦች በበዓል ቀን በመዝሙር እንደሚያደርጉት፥ እርሱ በአንቺ ይደሰታል።”
እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል።
በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።
እኔ እንድኖርባት ወደ ተቀደሰችው ከተማዬ ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ የታመነች ከተማ በመሆን ትታወቃለች፤ እኔ የሠራዊት አምላክ የምኖርበት ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ተብሎ ይጠራል፤
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ በፊቴ መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ በእርሱ የምትደሰቱበት የቃል ኪዳን መልእክተኛም በእርግጥ ይመጣል።”
“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።
ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ ሰባቱን ኮከቦች በቀኝ እጁ ከያዘውና በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል ከሚመላለሰው የተነገረ ነው፤
እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤