Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 31:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣ በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣ በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህም አያዝኑም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ እልል ይላሉ፥ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ፥ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:12
35 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።


“በዚያን ጊዜ ተራራዎችም ሁሉ በወይን ተክል ይሸፈናሉ፤ በኰረብቶችም ላይ ብዙ ወተት የሚሰጡ ከብቶች ይሰማራሉ፤ በይሁዳ ምድር የሚገኙ ወንዞች ሁሉ በውሃ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ምንጭ ይፈልቃል፤ የሺጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።


እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።


እንዲሁም እናንተ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እኔ እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።


የምተክለው በእስራኤል በሚገኝ በከፍተኛ ተራራ ላይ ነው፤ ይህንንም የማደርገው ቅርንጫፎችን አስገኝቶ ፍሬ በማፍራት የተዋበ የሊባኖስ ዛፍ እንዲሆን ነው። በሥሩም የተለያዩ ወፎች ይኖሩበታል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ክንፍ ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ ጎጆዎቻቸውን ይሠሩበታል።


እኔም ራሴ በኢየሩሳሌምና በሕዝቤ ደስ ይለኛል፤ ከዚያም በኋላ ለቅሶም ሆነ የዋይታ ድምፅ አይኖርም።


እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ብርሃንሽ ስለሚሆን፥ ፀሐይሽ ከቶ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም ብርሃንዋን አትከለክልም፤ የመከራሽም ዘመን ያበቃል።


እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ላይ ይጠርጋል፤ የቀድሞው ሥርዓት ስላለፈ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ለቅሶ ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”


በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ይጠርግላቸዋል።”


ወይስ የእግዚአብሔርን የደግነቱንና የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ብዛት ትንቃለህን? እግዚአብሔር ደግነቱን ያበዛልህ አንተን ወደ ንስሓ ለመምራት እንደ ሆነ አታውቅምን?


ከዚህ ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ንጉሣቸው ወደ ዳዊት ይመለሳሉ፥ በኋለኛው ዘመን በፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ በረከቱንም ይቀበላሉ።


ነገር ግን አንተን እንድናከብርህ ኃጢአታችንን ይቅር ትልልናለህ።


ነገር ግን እኔ ልዑል እግዚአብሔር በሀገሪቱ ውስጥ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እስራኤላውያን በሙሉ ያመልኩኛል እላለሁ፤ እዚያ እቀበላቸዋለሁ፤ እንዲሁም በዚያ ምርጥ መባዎችንና የተቀደሱ ዕቃዎች ስጦታዎችን ከእናንተ እጠባበቃለሁ።


ስለዚህ አንተ እግዚአብሔር የተቤዠኻቸው እየዘመሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፤ ዘላቂ ደስታንም እንደ ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ሐሴትና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ግን ከእነርሱ ይወገዳል።


በመጨረሻም ቅጠሉ እንደ ረገፈ የወርካ ዛፍና ውሃ እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁ።


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ።


“እናንተ እምነት የማይጣልባችሁ ሕዝብ ሆይ! የእኔ ስለ ሆናችሁ ተመለሱ፤ ከእናንተ መካከል ከየአንዳንዱ ከተማ አንዳንድ፥ ከእያንዳንዱም ቤተሰብ ሁለት ሁለት መርጬ ወደ ጽዮን ተራራ አመጣችኋለሁ።


ጠባቂዎች በኤፍሬም ተራራ ላይ ሆነው ‘ኑ አምላካችን እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጽዮን እንሂድ’ የሚሉበት ጊዜ ይመጣል።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሕዝቦች ሁሉ ስለምትበልጥ ስለ እስራኤል በደስታ ዘምሩ፤ ‘እግዚአብሔር ሕዝቡን አድኖአል፤ በእስራኤል ምድር የቀሩትን ሁሉ ተቤዥቶአል’ እያላችሁ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።”


‘ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ የሕዝብ መኖሪያ ይሆናሉ፤ ምድርን የሚያርሱ ገበሬዎችና መንጋን የሚጠብቁ እረኞች በዚያ ይገኛሉ፤


የደከሙትን ሁሉ ኀይላቸው እንዲታደስ አደርጋለሁ፤ በረሀብ ዝለው የነበሩትንም ምግብ በመስጠት አጠግባቸዋለሁ፤


እንደገና በዚህች ምድር ቤቶችን፥ የእርሻ መሬቶችን፥ የወይን ተክል ቦታዎችን መግዛት የሚቻልበት ጊዜ ይመጣል ብሎአል።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝብም ሆነ እንስሳ የማይኖርባት ምድረ በዳ በሆነች በዚህች ምድር እንደገና እረኞች የበጎቻቸውን መንጋ የሚያሠማሩበት መስክ ይኖራል።


በተራራማው አገር በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ባሉ ከተሞች፥ በብንያም ክፍለ ግዛት፥ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉት መንደሮችና በይሁዳ የገጠር ከተሞች ሁሉ እረኞች እንደገና በጎቻቸውን ይቈጥራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


በመልካም መሰማሪያ ቦታ አሰማራቸዋለሁ፤ መሰማሪያቸውም በእስራኤል ተራራዎች ከፍተኛ ቦታ ይሆናል። በእስራኤል ተራራዎች ላይ ተመግበው በመልካም መሰማሪያ ቦታዎች ያርፋሉ።


አሁን ለዘር የሚሆን እህል በጐተራ ባይኖር የወይንና የበለስ፥ የሮማንና የወይራም ተክል ሁሉ ገና ፍሬ ባይሰጥም ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔ በረከትን እሰጣችኋለሁ።”


እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ በግልጽ ስለሚያዩ ከተማ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የደስታ መዝሙር ሲዘምሩ አድምጪ።


የዛፋችሁና የእርሻችሁ ፍሬ ሁሉ እንዲበዛ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እናንተን በአሕዛብ መካከል የሚያዋርድ ራብ አይደርስባችሁም።


እህላቸውን በሰላም ዘርተው ፍሬውን ይሰበስባሉ የወይን ተክሎቻቸውም ያፈራሉ። በቂ ዝናብ ስለሚዘንብ ምድሪቱ ብዙ ሰብል ትሰጣለች፤ ከስደት ለተረፉት ሕዝብ ይህን ሁሉ በረከት እሰጣለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios