Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 51:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ አንተ እግዚአብሔር የተቤዠኻቸው እየዘመሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ፤ ዘላቂ ደስታንም እንደ ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ሐሴትና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ግን ከእነርሱ ይወገዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፥ የዘላለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፥ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 51:11
29 Referencias Cruzadas  

አፋችን በሳቅ ተሞላ፤ አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤ በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን።


በእንባ የሚዘሩ የደስታ መዝሙር እየዘመሩ ይሰበሰባሉ።


እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል።


ልዑል እግዚአብሔር የሞትን ኀይል ለዘለዓለም ያጠፋል! ከሰዎችም ሁሉ ዐይን እንባን ያብሳል፤ ወገኖቹ በዓለም ሁሉ ላይ የተቀበሉትን ኀፍረት ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህን ተናግሮአል።


እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።


ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።


እንግዲህ ከባቢሎን ወጥታችሁ ሽሹ፤ “እግዚአብሔር አገልጋዩን እስራኤልን አድኖአል” የሚለውን የምሥራች ቃል በደስታ አብሥሩ፤ በየስፍራውም እንዲታወቅ አድርጉ።


እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚያጽናና እና ለሚሠቃዩትም ስለሚራራ ሰማያት ሆይ! ዘምሩ፤ ምድር ሆይ! ደስ ይበልሽ፤ ተራራዎች ሆይ! እልል በሉ።


“እናንተም ከባቢሎን በደስታ ወጥታችሁ፥ በሰላም ወደ ሀገራችሁ እንድትመለሱ ትደረጋላችሁ፤ ተራራዎችና ኰረብቶች በፊታችሁ በመዘመር ይፈነድቃሉ፤ የሜዳ ዛፎችም በእጆቻቸው ያጨበጭባሉ።


ኀፍረታቸው እጥፍ ስለ ነበረ፤ ውርደትም የእነርሱ ዕድል ፈንታ መሆኑ ስለ ታወጀ ስለዚህ ድርሻቸው እጥፍ ይሆናል፤ ዘለዓለማዊ ደስታም ያገኛሉ።


አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን ከልብ ሐዘን የተነሣ ታላቅሳላችሁ፤ ከመንፈስም ጭንቀት የተነሣ ዋይ፥ ዋይ ትላላችሁ።


እኔም ራሴ በኢየሩሳሌምና በሕዝቤ ደስ ይለኛል፤ ከዚያም በኋላ ለቅሶም ሆነ የዋይታ ድምፅ አይኖርም።


ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን


እንዳትወድቁ ሊያደርጋችሁና ነቀፋ የሌለባችሁ አድርጎ በደስታ በክብሩ ፊት ሊያቀርባችሁ ለሚችል፥


ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያይቱ ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።


እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ላይ ይጠርጋል፤ የቀድሞው ሥርዓት ስላለፈ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ለቅሶ ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”


ከእንግዲህም ወዲህ ምንም ዐይነት ርግማን አይኖርም፤ የእግዚአብሔርና የበጉ ዙፋን በከተማይቱ ውስጥ ይሆናል፤ አገልጋዮቹም ያመልኩታል።


በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ይጠርግላቸዋል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos