እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል” ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
ራእይ 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ |
እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል” ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥ ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፥ መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።
ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር።
ከስምዖን ነገድ በየትውልዳቸው በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው፥ እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነው ወደ ጦርነት ለመውጣት የሚችል ወንድ ሁሉ በየራሳቸው የተቈጠሩት፥
የይሁዳ ነገድ ሕዝቦች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ነገድ ሕዝቦች “ለእኛ ወደ ተደለደለው ርስት በከነዓናውያን ላይ ለመዝመት ከእኛ ጋር አብረን እንሂድ እኛም ለእናንተ ወደተደለደለው ርስት አብረን እንሄዳለን” አሉአቸው። የስምዖን ነገድ ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ሄዱ።