Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 29:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል” ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 አሁንም እንደ ገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት “ከእንግዲህ ባሌ ያቀርበኛል” አለች፤ ስለዚህ ሌዊ ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፥ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፥ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠ​ጋል፤ ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 29:34
11 Referencias Cruzadas  

እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።


በሦስተኛው ቀን ሰዎቹ ገና ከመገረዝ ቊስል ሳይድኑ ከያዕቆብ ልጆች መካከል ሁለቱ የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ ሰይፍ፥ ሰይፋቸውን ይዘው ማንም ሳያውቅባቸው፥ ወደ ከተማ ገቡና ወንዶቹን ሁሉ ገደሉ።


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።


አዳም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “በእግዚአብሔር ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” ስትል “ቃየል” የሚል ስም አወጣችለት።


የሌዊ ልጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ናቸው።


በዚያን ጊዜ ከሌዊ ነገድ የሆነ አንድ ሰው አንዲት ሌዋዊት ሴት አገባ፤


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos