Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የይሁዳ ነገድ ሕዝቦች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ነገድ ሕዝቦች “ለእኛ ወደ ተደለደለው ርስት በከነዓናውያን ላይ ለመዝመት ከእኛ ጋር አብረን እንሂድ እኛም ለእናንተ ወደተደለደለው ርስት አብረን እንሄዳለን” አሉአቸው። የስምዖን ነገድ ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የይሁዳም ሰዎች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ልጆች፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻችን ወደ ሆነው ምድር ዐብረን እንውጣ፤ እኛም እንደዚሁ ድርሻችሁ ወደ ሆነው ምድር ዐብረናችሁ እንወጣለን” አሏቸው፤ ስለዚህም የስምዖን ሰዎች ዐብረዋቸው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻዬ ወደ ሆነው ምድር አብረን እንውጣ፤ እኔም እንደዚሁ ድርሻህ ወደ ሆነው ምድር አብሬህ እወጣለሁ” አለው። ስለዚህም ከእርሱ ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሙን ስም​ዖ​ንን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም እን​ው​ጋ​ቸው፤ እኔም ደግሞ ከአ​ንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ስም​ዖ​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ ከነዓናውያንን እንወጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፥ እኔም ደግሞ ከአንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄዳለሁ አለው። ስምዖንም ከእርሱ ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 1:3
7 Referencias Cruzadas  

እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።


ኢዮአብም አቢሳይን እንዲህ አለው “ሶርያውያን ድል ሊያደርጉኝ መቃረባቸውን በምታይበት ጊዜ መጥተህ እርዳኝ፤ እኔም ዐሞናውያን አንተን ድል ሊያደርጉህ በሚቃረቡበት ጊዜ መጥቼ እረዳሃለሁ።


ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስቱም ለይሁዳ ነገድ እስከ ተመደበው ምድር ድረስ ገባ ያለ ነበር፤


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


የይሁዳ ሕዝብ ከስምዖን ሕዝብ ጋር በአንድነት ዘምተው በጸፋት ከተማ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ድል አደረጉ፤ ከተማይቱንም ፈጽመው ካጠፉአት በኋላ “ሖርማ” ብለው ሰየሙአት፤


እግዚአብሔርም “የይሁዳ ነገድ ተቀዳሚ ሆኖ ይዝመት፤ እኔ ምድሪቱን ለእነርሱ አሳልፌ እሰጣለሁ” አለ።


ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos