ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
መዝሙር 92:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ አውታር በሆኑት የሙዚቃ መሣሪያዎችና በበገና ቅኝት አንተን ማመስገን እንዴት መልካም ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥር አውታር ባለው በገና፣ በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ። |
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
ዳዊት “በገና፥ መሰንቆና ጸናጽል በመሳሰሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ የደስታ መዝሙሮችን ይዘምሩ ዘንድ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ሌዋውያንን ሹሙአቸው” በማለት የሌዋውያኑን መሪዎች ተናገረ፤
ዘወትር ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ነገር በሚቃጠልበት በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻና በሌሎችም በዓላት እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር የእነርሱ ተግባር ነበር፤ በየጊዜው ይህን አገልግሎት የሚፈጽሙ ሌዋውያን ቊጥራቸው ምን ያኽል መሆን እንደሚገባው ደንቦች ነበሩ፤ ሌዋውያን እግዚአብሔርን ለማምለክ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ለሁልጊዜ ተመድበዋል።
ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በማጀብ በአባታቸው መሪነት ጸናጽል ያንሿሹና መሰንቆና በገና ይደረድሩ ነበር፤ አሳፍ፥ ይዱታንና ሄማን በንጉሡ ሥልጣን ሥር ነበሩ።
ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ የመጨረሻው አንድ ሦስተኛ እጅ የመሠረት ቅጽር በር ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ ይጠብቅ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ ይሰብሰቡ፤
ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔር በነቢዩ ጋድና በነቢዩ ናታን አማካይነት ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውንና ዳዊትም ተግባራዊ ያደረገውን ትእዛዝ በመከተል በበገና፥ በጸናጽልና በመሰንቆ የሠለጠኑ ሌዋውያንን በቤተ መቅደሱ ውስጥ መደበ፤
የኢየሩሳሌም ከተማ ቅጽር የምረቃ በዓል በተከበረበት ዕለት ሌዋውያኑ በጸናጽል፥ በበገናና በመሰንቆ በዓሉን እንዲያከብሩ ከየሚኖሩበት ስፍራ ተፈልገው መጡ።
ከዚያም አልፈህ የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር ወደሚገኝበት ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ ወደ ከተማይቱም መግቢያ በር በምትደርስበትም ጊዜ በኮረብታው ላይ መሥዋዕት አቅርበው የሚመለሱ የነቢያትን ጉባኤ ታገኛለህ፤ እነርሱም በገና እየደረደሩ፥ ከበሮ እየመቱ፥ ዋሽንት እየነፉ፥ በመሰንቆ ዜማ ሲዘምሩና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ትንቢት ሲናገሩ ታገኛቸዋለህ።