መዝሙር 92:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ማመስገንና የምስጋና መዝሙር ለአንተ ማቅረብ መልካም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብሩንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምንም እንዳትናወጥ አጸናት። |
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በሚመሰክሩት ከንፈሮች የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ነው።