Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 57:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ለዘ​ለ​ዓ​ለም በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን የሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳን አድሮ የሚ​ኖር፥ ለተ​ዋ​ረ​ዱት ትዕ​ግ​ሥ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ልባ​ቸ​ውም ለተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 57:15
72 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከለና ለዘለዓለማዊው አምላክ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤


“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ?


እኔ ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን እንዴት እንደምቀጣ በሰማህ ጊዜ፥ ራስህን አዋርደኽ በሐዘን ልብስህን በመቅደድና በማልቀስ ንስሓ ገብተሃል፤ ስለዚህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።


እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳል፤ ትሑታንን ግን ያድናቸዋል።


የቅዱሱን ቃል ምንጊዜም ስላልካድኩ፥ ምንም እንኳ ሥቃይ ቢበዛብኝ በደስታ በዘለልኩ ነበር።


ለድኾች በልግሥና ይሰጣል፤ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳኑንም ሰጠ፤ ስሙም ቅዱስና አስፈሪ ነው።


አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።


እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ በሰማይ ወደ ሆነው ወደ አንተ እመለከታለሁ።


ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክ ሆነህ ሳለ፥ ትሑታንን ትንከባከባለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ሆነህ ትመለከታቸዋለህ።


መከራ ዙሪያዬን በሚከበኝ ጊዜ መከታ ሆነህ በሕይወት ትጠብቀኛለህ፤ በቊጣ የተነሡብኝ ጠላቶቼን ትቃወማቸዋለህ፤ በኀይልህም ትታደገኛለህ።


ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፤ ቊስላቸውንም ይጠግናል።


ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።


ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።


ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት የተሰበረ ልብ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።


በዚያን ጊዜ በትክክለኛ መሥዋዕትና በሚቃጠል መሥዋዕት ትደሰታለህ፤ እኛም በመሠዊያህ ላይ እንደገና ኰርማዎችን እናቀርባለን።


በምድር ሁሉ ላይ ጌታና ሁሉን ቻይ አምላክ አንተ እግዚአብሔር እንደ ሆንክ ይወቁ።


ተራራዎችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት፥ አንተ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላክ ነህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘመናት ሁሉ በፊት አምላክ ነህ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል አምላክ ነህ፤ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በሥልጣንህ ሥር ናቸው።


የአንተን ታላቅና አስፈሪ ስም ያመስግኑ! እርሱ ቅዱስ ነው።


“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?


በማይለወጥ ፍቅርህ ያዳንካቸውን ሕዝብ መራህ፤ በብርታትህም ወደ ተቀደሰችው ምድር እንዲገቡ አደረግህ፤


እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።


ከዚህ በኋላ ድንኳኑ በደመና ተሸፈነ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ድንኳኑን ሞላው።


ደመናው ስለረበበበትና የእግዚአብሔርም ክብር ድንኳኑን ስለ ሞላው ሙሴ ወደ ድንኳኑ ለመግባት አልቻለም።


ከትዕቢተኞች ጋር የዘረፉትን አብሮ ከመካፈል ትሑት ሆኖ በድኽነት መኖር ይሻላል።


ዓለም ከመፈጠርዋ አስቀድሞ፥ ከዘመናት በፊት ተሾምኩ።


እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፦ “በቀትር ጊዜ በጸጥታ እንደምታበራ ፀሐይ፥ በመከርም ወራት በሞቃት ሌሊት እንደሚታይ ጤዛ ከሰማያዊ መኖሪያዬ ጸጥ ባለ መንፈስ ቊልቊል እመለከታለሁ።


እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው! በሰማያትም ይኖራል፤ ለጽዮንም ጽድቅንና ፍትሕን ያጐናጽፋል።


ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤ እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤ ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አገልጋዬ ሥራው ሁሉ ይከናወንለታል፤ በክብርም እጅግ ከፍ ከፍ ይላል።


ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን አየሁት፤ እርሱም ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።


አንዱ መልአክ ከሌላው ጋር በመቀባበል፥ “የሠራዊት አምላክ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ነው! ክብሩም በዓለም ሁሉ የተሞላ ነው!” ይሉ ነበር።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ከተቀደሰውና ከክቡር መኖሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህ የት አሉ? መልካም ፈቃድህና ርኅራኄህስ የት አለ? እነርሱ ከእኛ ርቀዋል።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።


በሰማይ ወዳለው አምላካችን ልባችንንና እጃችንን እናንሣ።


ይህንንም የማደርገው፥ ለፈጸምሽው በደል ሁሉ ይቅርታ ሳደርግልሽ ሥራሽን በማስታወስ በድንጋጤ ዐፍረሽ ጸጥ እንድትዪ ነው፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


“በመላዋ ኢየሩሳሌም ከተማ ተዘዋወር፤ በከተማይቱ ከተፈጸመውም አጸያፊና አሳፋሪ ነገር የተነሣ በመሠቀቅ ባዘኑት ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት አድርግባቸው!” አለው።


ንጉሥ ሆይ! አንተ ለምታቀርበው ከባድ ጥያቄ ከአማልክት በቀር መልስ መስጠት የሚችል የለም፤ አማልክት ደግሞ በሰው መካከል የሚኖሩ አይደሉም።”


ውሳኔውም የተላለፈው በቅዱሳን መላእክት ነው፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ላይ ሥልጣን ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቅ ነው፤ ሥልጣኑንም ለፈቀደለት ሰው ይሰጠዋል፤ የተናቁትንም በሥልጣን ላይ ያስቀምጣቸዋል።’


ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


ሐዘናችሁን ለመግለጽ ልብሳችሁን መቅደድ ብቻ በቂ አይደለም፤ ይልቅስ ልባችሁንም በመስበር ንስሓ ግቡ” እግዚአብሔር አምላካችሁ ቸር፥ መሐሪ፥ ለቊጣ የዘገየ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የበለጸገና ለቅጣት የዘገየ በመሆኑ ወደ እርሱ ተመለሱ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”


እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ መኖሪያው ለመምጣት ስለ ተነሣ ሁላችሁም በፊቱ ዝም በሉ።


ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።


ስለዚህ እናንተ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይመስገን፤


ኀያሉ እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጎልኛልና። ስሙም ቅዱስ ነው።


“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤


እናንተ ቅዱሱንና ጻድቁን ‘አንፈልገውም’ ብላችሁ አንድ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።


ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለሰዎች የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፥ ይኸውም ዘለዓለማዊው ኀይሉና አምላክነቱ እርሱ በፈጠራቸው ነገሮች አማካይነት ግልጥ ሆኖ ስለ ታየ ሰዎች ለሚያጠፉት ጥፋት ምክንያት የላቸውም።


እኛ ከእግዚአብሔር በምናገኘው መጽናናት በመከራ ላይ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንድንችል እግዚአብሔር እኛን በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።


ስለዚህ ይህ ሰው በጣም ከማዘኑ የተነሣ ተስፋ እንዳይቈርጥ ይልቅስ ይቅርታ እንድታደርጉለትና እንድታጽናኑት ይገባል።


ነገር ግን የተዋረዱትን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን።


ዘለዓለማዊ አምላክ መጠጊያህ ዘለዓለማዊ ክንዶቹ ደጋፊዎች ናቸው፤ ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤ እንድትደመስሳቸውም ያደርጋል።


ስለዚህ ለዘለዓለማዊው ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ለአንዱ አምላክ ክብርና ምስጋና ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ክብርና ዘለዓለማዊ ኀይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


በዘለዓለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር የሌለበት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናገለግል ኅሊናችንን ከሞተ ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን!


ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”


“ለፊላደልፍያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።


አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች ነበሩአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ሌሊትና ቀን፦ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፥ የነበረ፥ ያለና የሚመጣውም” ከማለት አያቋርጡም ነበር።


“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችንን የሚመስልም መጠጊያ ምሽግ የለም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos