መዝሙር 79:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን? ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድድ ይኖራልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ። |
“በኀይለኛ ቅናቴ በሌሎች ሕዝቦች ላይና በመላዋ ኤዶም ላይ እናገራለሁ፤ እነርሱ ደስታን በተመላ ስሜትና በፍጹም ንቀት መሰማሪያዋን ለመውረር ምድሬን ርስታቸው አደረጉት፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ጥቂት ታገሡ፤ በእነርሱ ላይ የምፈርድበት ጊዜ ይመጣል፤ ሕዝቦችንና መንግሥታትን ሰብስቤ ኀይለኛ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ከቊጣዬም ኀይለኛነት የተነሣ መላዋ ምድር ትጠፋለች።
መልአኩም “የሠራዊት አምላክ ሆይ! ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ከተቈጣህ እነሆ ሰባ ዓመቶች አለፉ፤ ምሕረት የማታደርግላቸው እስከ መቼ ነው?” ሲል ጠየቀ።
እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።
በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።